Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

በአፍሪካ የመጀመሪያ ደረጃ የጤና አገልግሎትን በዲጂታል ለማዘመን የሚያስችል አህጉር አቀፍ ወርክሾፕ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ

CERPHI

የጤና ስርዓትን ለማዘመን እና ጥራት ያለው አገልግሎትን ለሁሉም ተደራሽ ለማድረግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ ወሳኝ መሣሪያ መሆኑን የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ በፕሮግራሙ መክፈቻ ንግግራቸው ገልጸዋል።

ይህንን አህጉራዊ ራዕይ ከግብ ለማድረስ፣ የአፍሪካ በሽታ መከላከልና መቆጣጠር ማዕከል (Africa CDC) ከቴክኒክ ቡድኖች እና አጋር አካላት ጋር በመሆን ያዘጋጀው “የመጀመሪያ ደረጃ የጤና አገልግሎት ዲጂታላይዜሽን ማዕቀፍ (PHC Digitalization Framework)” ረቂቅ ሰነድ በአዲስ አበባ እየተገመገመ ይገኛል። ማዕቀፉ አህጉሪቱ በተበታተኑ የዲጂታል መተግበሪያዎች ፋንታ የተቀናጀ፣ ግልጽነት የሰፈነበት እና በመረጃ ላይ የተመሰረተ ውሳኔ ሰጪነትን የሚያሰፍን የዲጂታል ጤና ስነ-ምህዳር እንድትገነባ መንገድ የሚከፍት ዶ/ር መቅደስ ተናግረዋል።

የአፍሪካ ሲዲሲ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ጃን ካሴያ በአዲስ አበባ እየተካሄደ በሚገኘው ዓለም አቀፍ መድረክ ላይ ባደረጉት ንግግር፤ አፍሪካ ከጥገኝነት በመውጣት የራሷን የጤና ዕጣ ፈንታ በራሷ ለመወሰን የሚያስችሏትን ስትራቴጂካዊ ተግባራት እያከናወነች መሆኑን ገልጸው፣ ኢትዮጵያ ለዚህ ታሪካዊ ሽግግር ተጠቃሽ አርአያ መሆኗን አረጋግጠዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የአፍሪካ የዲጂታል ጤና እና የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ሻምፒዮን ሆነው መሾማቸው ለአህጉሪቱ ትልቅ ፋይዳ እንዳለው የጠቆሙት ዳይሬክተሩ፤ እስከ 2035 ድረስ 90 በመቶ የሚሆኑ የአፍሪካ የጤና ተቋማትን በዲጂታል ቴክኖሎጂ ለማስተሳሰር የተቀመጠው ግልጽ ራዕይ ከግብ እንዲመታ በቁርጠኝነት እንደሚሰራ ጠቁመዋል።

​የወርክሾፕ ዋና ዓላማ ከመላው አህጉሪቱ የተሰባሰቡ ባለሙያዎች የቀረበውን ማዕቀፍ በጥልቀት በመገምገም በተግባር ሊተረጎምና ሊቀናጅ የሚችል ዘላቂነት ያለው ሰነድ ማዘጋጀት ሲሆን በውይይቱ ማጠቃለያ ላይ የሚጸድቀው ማዕቀፍ፣ በመላው አፍሪካ የሚገኙ የመጀመሪያ ደረጃ የጤና ተቋማት በቴክኖሎጂ ታግዘው የተሻለ የጤና ውጤት እንዲያስመዘግቡ መሪ ሆኖ ያገለግላል። ይህም ጠንካራ የጤና ስርዓት በመገንባት ጤናማ አህጉርን ለመፍጠር ለሚደረገው ጉዞ ከፍ ያለ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ተጠቁሟል።

Website: moh.gov.et

Facebook: Ministry of Health,Ethiopia

Twitter: x.com/fmohealth

YouTube: youtube.com/@FMoHealthEthiopia

Tiktok: tiktok.com/@mohethiopia

Telegram: t.me/M0H_EThiopia

Linkedin: lnkd.in/ewFJ6VAB

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *