Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የወረርሽኝ ቁጥጥር ስራ ውጤት እያመጣ መሆኑ የክልሉ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አሳወቀ ።

CERPHI

በክልሉ ለሚገኙ ጤና ጣቢያ የድንገተኛ አደጋዎች ቅኝት እና ምላሽ ባለሙያዎች መሰረታዊ አደጋዎች ቅኝት እና ምላሽ ስልጠና በወራቤ መስጠት ተጀመረ ፡፡

ስልጠናውን በንግግር ያስጀመሩት የክልሉ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ማሙሽ ሁሴን በክልሉ የወረርሽኝ ቁጥጥር ስራዎች ውጤት እያስገኘ መሆኑን ገልጸዋል ፡፡

በጤና ተቋም ያሉ የድንገተኛ አደጋዎች ቅኝት እና ምላሽ ባለሙያ የወረርሽኝ ቁጥጥር ስራን በጤና ተቋም ለማጠናከር ሰልጣኞቹ በተለዩ 36 በሽታዎች ዙሪያ ምንነታቸውን ፣ ምልክቶች ፣ የልየታ ስርዓት ፣ የመረጃ ልውውጥ እና የሪፖርት ስርዓት ላይ መሰረታዊ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑን ጠቁመዋል ፡፡

በጤና ተቋም ደረጃ የወረርሽኝ ቁጥጥር ስራን ለማጠናከር የጤና ተቋማት የሚገኙ የድንገተኛ አደጋዎች ባለሙያዎችን አቅም ማሳደግ ትኩረት እንደተሰጠው አስታውዋል ፡፡

በጤና ተቋማት የሚገኙ የድንገተኛ አደጋዎች ቅኝት እና ምላሽ ባለሙያዎች አቅም አለመጠናከር ፣ ስራውን ባለቤት ሆኖ አለመፈጸም ተግዳሮት መሆኑ የገለጹት አቶ ማሙሽ በቀጣይ ስራውን በእውቀት በኃላፊነት ለመስራት ስልጠናው ጠቃሚ ነው ብለዋል ፡፡

ስልጠናው ለተከታታይ ቀናት በክልሉ በተለያዩ ክላስተሮች እንደሚሰጥ ተገልጿል ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *