Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አምስተኛ ዙር የተቀናጀ የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ በይፋ ተጀመረ።

CERPHI

ክልላዊ የተቀናጀ የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ በይፋ የተጀመረው በሀዲያ ዞን ሌሞ ወረዳ በማስቢራ ቀበሌ ነው።

ዘመቻውን በይፋ ያስጀመሩት በክልሉ ጤና ቢሮ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ለገሰ ጴጥሮስ በዚህ ጊዜ እንዳሉት በክልሉ ከዚህ በፊት በተካሄዱ ዘመቻዎች የጤናውን ዘርፍ ልያሻሽሉ የምችሉ ውጤቶች ተመዝግቧል።

አቶ ለገሰ፦ ህጻናት መውሰድ ያለባቸውን ክትባት ባለመውሰዳቸው ለኢኮኖሚ ችግር ስለሚጋለጡ የአከባቢው ህብረተሰብ ለዘመቻው ትኩረት እንዲሰጥ አጽንኦት ሰጥተዋል።

በዘመቻው ያልተከተቡ፣ ጀምረው ያቋረጡ ህጻናትን በመለየት የአገልግሎት ተጠቃሚ ማድረግ የባለድርሻ አካላት ሚና እንደሆነም ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ አስረድተዋል።

በዚህም የላንቃና የከንፈር መሰንጠቅ፣ የማህጻን ውልቃትና በፌስቱላ የተጠቁ እናቶችን በመለየት ህክምና አገልግሎት ማግኘት እንድችሉ ማድረግ ያስፈልጋል ሲሉም ተደምጠዋል አቶ ለገሰ።

በዘመቻው በክልል ደረጃ ከ1 ነጥብ 4 ሚሊዮን ከ5 ዓመት በታች የሆኑ ህጻናት የፕሮግራሙ ተጠቃሚ እንደሚሆኑም አብራርተዋል።

የሀዲያ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ ዶክተር ደሳለኝ ሽጉጤ በበኩላቸው ዘመቻው ውጤታማ እንዲሆን አስፈላጊ ቅድመ ዝግጅት መደረጉን ተናግረዋል።

የነገ ሀገር ተረካቢ ትውልድ ለመፍጠር የህጻናት ጤና ትልቁን ድርሻ የሚወስድ በመሆኑ ህብረተሰቡ ልጁን በማስከተብ ግዴታውን ሊወጣ ይገባል ብለዋል ኃላፊው።

በዘመቻው ማስጀመሪያ የጤና ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ፣የአለም ጤና ድርጅት ፣ የዩኒሴፍ ፣ አፍሪኔት ተወካዮች ተገኝተዋል ፡፡

አብርሃም ሙጎሮ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *