Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

ለኢትዮጵያ የድንገተኛ ህክምና ቡድን (EMT) የአመራር ክህሎት ስልጠና ተሰጠ::

CERPHI

የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት (EPHI) ከUK-MED ጋር በመተባበር ከፌዴራል፣ ከክልሎች እና ከመከላከያ ለተውጣጡ 25 የድንገተኛ ህክምና ቡድን አስተባባሪዎች የሰጠው የአመራር ክህሎት ስልጠና ተጠናቋል።

ይህ ስልጠና በድንገተኛ የህብረተሰብ ጤና አደጋዎች ወቅት የሚሰጠውን የህክምና ምላሽ በብቃት ለመምራት እና የማስተባበር አቅምን ለማሳደግ ያለመ ሲሆን ከUK-MED ባለሙያዎች ጋር ልምድ ልውውጥ የተደረገበትና ሀገራዊ የድንገተኛ ህክምና ምላሽ ዝግጁነትን የሚያጠናክር ነው።

ስልጠናው በንድፈ-ሀሳብ ብቻ ሳይወሰን እንደ Tabletop Exercise ያሉ ተግባራዊ ሞዴሎችን በመጠቀም የተከናወነ ሲሆን በዋናነትም በድንገተኛ አደጋ ወቅት የሚታዩ ጫናዎችን የመቋቋም፣ የውሳኔ አሰጣጥ፣ የቡድን ስምሪት፣ ዝግጅት እና የተልዕኮ ማጠናቀቂያ ሂደቶች ላይ ትኩረት አድርጓል።

በተጨማሪም ደህንነቱ የተጠበቀ የስራ አካባቢን መፍጠር ፣ የባህል ብዝሃነትን ያከበረ የስራ ግንኙነት እና የጋራ ትብብርን ማጠናከር በስልጠናው በስፋት ተዳስሰዋል። ይህ ስልጠና በኢትዮጵያ የድንገተኛ ህክምና ምላሽ ዝግጁነትን ከዓለም አቀፍ ደረጃ ጋር ለማጣጣምና ሀገራዊ አቅምን ለመገንባት ትልቅ ሚና ይጫወታል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *