Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

የአፍሪካን የወደፊት እጣ ፈንታ ለመወሰን በሴቶች፣ ህጻናት እና ወጣቶች ጤና ላይ ኢንቨስት ማድረግ ያስፈልጋል::

CERPHI

ከ39ኛው የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ ጎን ለጎን በሴቶች፣ ህጻናትና ወጣቶች ጤና ዙሪያ ከፍተኛ የሚኒስትሮች እና አጋሮች ውይይት ተካሄደ።

​የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ በ39ኛው የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ ጎን ለጎን በተካሄደው የሚኒስትሮች እና አጋሮች ውይይት ተገኝተው ባስተላለፉት መልልዕክት፣ የአፍሪካን የወደፊት እጣ ፈንታ ለመወሰን በሴቶች፣ህጻናት እና ወጣቶች ጤና ላይ ኢንቨስት ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል።

አፍሪካ የአለማችን ብዙ ወጣት የሚኖርባት አህጉር መሆኗን የገለጹት ዶ/ር መቅደስ፣ ዛሬ በጤና እና በሥርዓተ ምግብ ላይ የምናደርገው ኢንቨስትመንት የአህጉሪቱን የረጅም ጊዜ ብልጽግና የሚያረጋግጥ ነው ያሉት ሚኒስትሯ ​በጤናው ዘርፍ የሚታዩ እንደ ግጭትና የፋይናንስ እጥረት ያሉ ተግዳሮቶችን ለመፍታት የመንግስትና የግል ዘርፍ አጋርነት (PPP) ትልቅ ሚና እንዳለው ጠቁመዋል።

​የUNFPA ዋና ዳይሬክተር ዲየን ኬይታ በበኩላቸው፣ አፍሪካ ከድህነት ወደ ብልጽግና የምታደርገው ጉዞ ስኬታማ የሚሆነው እናቶች በምጥ የማይሞቱባትንና ህጻናት መከላከል በሚቻል በሽታ የማይቀጠፉባትን አህጉር መገንባት ሲቻል መሆኑን ገልጸዋል።

​በመጨረሻም የአፍሪካ ሀገራት የጤና በጀታቸውን እንዲያሳድጉና የጤና ስርዓቱን በሀገር በቀል እቅዶች እንዲመሩ ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን በተለይም የአዋላጅ ነባሪዎችን ቁጥር መጨመርና የጤና ቁሳቁሶችን በአህጉሪቱ ውስጥ ማምረት ለዘላቂ ለውጥና ለኢኮኖሚ እድገት ወሳኝ መሆኑ ተመላክተዋል።

Website: moh.gov.et

Facebook: Ministry of Health,Ethiopia

Twitter: x.com/fmohealth

YouTube: youtube.com/@FMoHealthEthiopia

Tiktok: tiktok.com/@mohethiopia

Telegram: t.me/M0H_EThiopia

Linkedin: lnkd.in/ewFJ6VAB

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *