
በክልሉ በስድስተኛ ሳምንት የወባ ጫናን ጨምሮ ሌሎች ተላላፊና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ላይ የተከናወኑ ቅኝትና ምላሽ ተግባራት ሪፖርት ቀርቦ ሰፊ ዉይይት ተደርጎባቸዋል ።
የክልሉ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ለገሰ ጴጥሮስ በዚህ ወቅት እንደተናገሩት በቀጣይ የቀልግ ዝናብን ተከትሎ ዝቅተኛ የወባ ስርጭት ለሚከሰትባቸው ወራቶች አስመልክቶ ከወዲሁ ቅድመ ዝግጅት መደረግ እንደሚገባው አስታውቀዋል ፡፡
ከስርዓተ ምግብ ክፍተት ጋር ተያይዞ የሚከሰቱ የአጣዳፊ የምግብ እጥረት ችግሮችን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር በየመዋቅሩ የቅኝትና በተቋማት ደረጃ የአገልግሎት አሰጣጥ እንዲሁም ከባለድርሻ አካላት ጋር ቅንጅታዊ አሰራሮችን አጠናክሮ መስራት እንደሚገባ ተገልጿል ፡፡
በክልሉ የነጻ የስልክ ጥሪ 6427 አማካኝነት እንዲሁም ኢንስቲትዩቱ በዘረጋቸው በተለያዩ መንገዶች የሚሰጡ የድንገተኛ ጤና አደጋ ጭምጭምታዎች እና ጥቆማዎች መነሻ ያደረገ የቅኝት ስራዎች ተጠናክረው እየተሰሩ መሆናቸው ተገልጿል።




