Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

የፕላዝሞዲየም ቫይቫክስ ወባን በተገቢ የጨርሶ ማዳን ህክምናን በጂሲክስፒዲ ምርመራ ውጤት ላይ በመመስረት የማክም ዘዴ የትግበራ ጥናት

በጋምቤላ እና በደቡብ ኢትዮጵያ ክልሎች ሲካሄድ የቆየው የፕላዝሞዲየም ቫይቫክስ ወባን ጨርሶ ማዳን ህክምና የትግበራ ጥናት ውጤታማ በሆነ መልኩ መጠናቀቁ ተገለፀ። ይህ ፕሮጀክት፣ የታካሚዎችን የጂሲክስፒዲ ኢንዛይም መጠን በመመርመር ላይ የተመሰረተ የህክምና ዘዴን ተግባራዊነት በጤና ስርአቱ የተለያዮ ደረጃዎቸ፣ የሙያተኞች የትምህርት ዝግጅት፣ የተልያየ የቫይቫክስ ወባና የጂሲክስፒዲ የዘረመል ለውጥ ምጣኔ ባለባቸው አካባቢዎች የተካሄደ ጥናት ነው።

የዚህ ጥናት አላማ በጤና ስርአቱ ውስጥ የተለያዩ ደረጃዎች (አጠቃላይ ሆስፒታሎች፣ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታሎችና የጤና ጣቢያዎች) እንዲሁም የተለያየ የትምህርት ዝግጅት ደረጃ (የህክምና ዶክተሮች፣ ጤና መኮንኖች፣ ነርሶች፣ የላብራቶሪ ቴክኒሻኖችና ፋርማሲስቶች) ባላቸው የጤና ባልሙያዎቸ የጂሲክስፒዲ ኢንዛይምን ውጤታማ ምጣኔን አስቀድሞ በመለካት ተገቢውን አማራጭ የ”ፕሪማክዊን” ወይም “ታፌኖክዊን” መድኃኒቶችን ሊያስከትሉ የሚችሉትን በቀይ የደም ሴሎች ጉዳት ምክንያት ሊያጋጥም የሚችልን በሰውነት ውስጥ የደም መፍሰስ አደጋ በእጅጉ ለመቀነስ ብሎም በማስቀረት ደህንነቱ የተጠበቀ ህክምና መስጠት ነው።

ይህ በሦስት ምዕራፎች የተከፈለው ጥናት በነሐሴ ወር 2016 ዓ.ም ተጀምሮ እስከ ህዳር 2018 ዓ.ም ድረስ የቆየ ሲሆን በሁለቱም ክልሎች በአጠቃላይ 12 የጤና ተቋማት ላይ ተግባራዊ ሆኗል። በጥናቱ ሂደትም የጤና ባለሙያዎች በጥቅሉ 93% ትክክለኛውን ቫይቫክስ ወባን ጨርሶ ማዳን ህክምና ሰጥቷል።

በጥናቱ ግብረ መልስ ውይይቶች ላይ የጥናቱ የመጨረሻ ግኝቶች በአርባ ምንጭ ከተማ ከፌዴራል፣ ከክልል እና ከዞን የተወከሉ የጤና ስርአቱ አመራሮች/አማካሪዎች ባሉብት ውይይት ተደርጎባቸዋል። በተመሳሳይ በሳውላ ከተማ ከማህበረሰብ ተወካዮች፣ ከሃይማኖት አባቶች እና ከአጋር አካላት ጋር በተደረገው ውይይት በማህበረሰቡና የጤና ስርአቱ ተውካዮች የጥናቱ ውጤት ወቅቱን የጠበቀና አስፈላጊ መሆኑ ተናግረዋል፡፡

የዚህ ጥናት ውጤታማነት በቀጣይ በጤና ስርአቱ ውስጥ መተግበር እንዲቻል በፖሊሲ መደገፍ ስላለበት በሃገር አቀፍ ደረጃ ተመሳሳይ በጥናቱ ውጤት ላይ ውይይት መደረግና የፖሊሲ ምክረ-ሃሳብ መቅረብ እንደሚገባ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡

LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/106861043/admin/dashboard/

Website:

Facebook: https://web.facebook.com/AHRIGovEt/?_rdc=1&_rdr#

Youtube: https://www.youtube.com/@armauerhansenresearchinsti218

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *