Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

የማእከላዊ ኢትዮጺያ ክልል በክልሉ ጤና ቢሮ ጤናና ጤና ነክ አገልግሎቶች ግብዓት ጥራት ቁጥጥር ባስልጣን በጤና ነክ ተቋማት ቁጥጥር ለሚሰማሩ ተቆጣጣሪዎች ስልጠና በመስጠት ተጀመረ ።

የጤና ነክ ተቋማት ዳሰሳና ቁጥጥር ስራ ለይ ለሚሰማሩ ተቆጣጣሪ ባለሙያዎች ለሁለት ቀናት የሚቆይ ዓቅም ማጎልበቻ ስልጠና አየሰጠ መሆኑን ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ አስታውቋል ።

የጤናና ጤና ነክ አገልግሎቶች ግብዓት ጥራት ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዬጎሬ ዳቆሮ በስልጠናው ማስጀመሪያ ባስተላለፉት መልዕክት የጤና ነክ ተቋማት የማህበረሰቡን የጤና ተጠቃሚነት ከማረጋገጥ አኳያ ከሚያበረክቱት አስተዋጽኦ ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ትኩረት ይሻሉ ብለዋል።

የጤና ነክ ተቋማት ብቃት፣ ጥራት፣ ደረጃና ንጽህናውን የጠበቀ አገልግሎት በቀጥታ ከማህበረሰቡ ጤና ጋር የሚቆራኝ መሆኑንም ተናግረዋል ።

የተቋማት ክፍተትና ከደረጃ በታች መሆን ምክንያት የህብረተሰቡ ጤና ችግር ውስጥ እንዳይገባ ለማድረግ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ተግባራትን በትልቅ ኃላፊነት አየፈጸመ ስለመሆኑም አቶ ዬጎሬ ገልጸዋል።

በክልሉ ጠንካራ የጤናና ጤና ነክ ተቋማት ቁጥጥር ስርኣት ለመዘርጋት እየተሰራ መሆኑን ያመላከቱት ዳይሬክተሩ ወቅቱን የሚመጥን የቴክኖሎጂ የአሰራር ስርዓቶችን በመከተል ከወረቀት ንክኪ ነጻ የሆነ የቁጥጥር ስራ ለመስራት የሚያስችሉ ጥሩ ጅምሮች መኖራቸውን አስገንዝበዋል።

የዞንና ልዩ ወረዳ እንዲሁም ከተማ አስተዳደር የጤናና ጤና ነክ ተቋማት ቁጥጥር ባለሙያዎችና አስተባባሪዎች የስልጠናው ተሳታፊዎች መሆናቸው ታውቋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *