
(ሆሳዕና፦ ጥር 20/2018) በክልሉ ጤና ቢሮ ”ጠንካራ የአመራር ግንባታ ለውጤታማ የጤና ስርዓት” በሚል መሪ ቃል በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ሲሰጥ የቆየው የመጀመሪያ ዙር የጤናው ዘርፍ የአመራር አቅም ማጎልበቻ ስልጠና ተጠናቋል።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ለ276 ሰልጣኞች ለተከታታይ 7 ቀናት ሲሰጥ የቆየው የመጀመሪያ ዙር የጤናው ዘርፍ የአመራር አቅም ማጎልበቻ ስልጠና ተጠናቋል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ እንደተናገሩት ዘላቂ የጤና ልማት ስርዓትን ለመዘርጋት የጤናው አመራር ስልጠና ወሳኝ ነው ብለዋል።
እንደ ክልል በሁሉም ዘርፍ የብልጽግና ማዕከል ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልፀው ይህንኑ በጤናው ዘርፍ ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሰራ ስለመሆኑም ገልፀዋል።
እውቀት ላይ የተመሰረተ አገልግሎት በመስጠት በጤናው ዘርፍ ተጠያቂነት እና ተአማኒነትን በማጎልበት ተግባራትን በኃላፊነት መወጣት ያስፈልጋል ብለዋል።
የጤናው ስርዓት ላይ ያጋጠሙ 15 ተግዳሮቶችን ለመፍታት የሚተገበሩ 12 ስትራቴጂክ መፍትሄዎችን በመለየት ወደ ስልጠና መገባቱን ገልፀው እነዚህም በአጭር፣ በመካከለኛ እና በረጅም ጊዜ መፍትሔ የሚሰጡ ስለመሆናቸውም ገልፀዋል።
ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ለጤናው ተግባር የሚውል ሀብት በመሰብሰብ ክፍተቶችን ለመሙላት የጋራ ዕቅድና ሀሳብ በማደራጀት የመሪነት ሚናቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል።
ተገልጋዮች በአገልግሎት አሰጣጥ ደስተኛ ሆነው እንዲመለሱ በተጠያቂነት፣ በኃላፊነት እና በቁርጠኝነት ለውጤታማነቱ እንዲረባረቡ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
በቀጣይ ጊዜን በአግባቡ በመጠቀም በጤናው ዘርፍ ለሚታዩ ችግሮች መፍትሄ በመስጠት ቅንጅታዊ ስራዎችን በማጠናከር በቤተሰብ ደረጃ የጤናን ብልጽግና ለማረጋገጥ ጠንክረው እንዲሰሩ አሳስበዋል።
ከልጠናው የህብረተሰቡን ጤና ለማሻሻል የሚያስችል በቂ እውቀት ክህሎት ማግኘት መቻላቸውን ሰልጣኞች ሰልጣኞች ተናግረዋል።
ለለውጥ ቁልፍ የሆነ ስልጠና መሰጣቱን የገለፁት ሰልጣኞቹ በተከታታይ 7 ቀናት በንድፍ ሀሳብ ያገኙትን እውቀት ተግባራዊ ለማድረግ ስለመዘጋጀታቸው ተናግረዋል።
በቀጣይ በየዘርፉ ስልጠና ያገኙ የጤናው ዘርፍ አመራሮች የአመራር ኃላፊነታቸውን በአግባቡ በመወጣት ለህብረተሰቡ ተጠቃሚነት በቁርጠኝነት እንደሚሰሩም ተናግረዋል።
በመጨራሻም ለስልጠና ውጤታማነት እና ስኬት ትብብር ያደረጉ አካላትን አመስግነው ለባለድርሻ አካላትና ሰልጣኞቹ የእውቅና እና የምስክር ወረቀት የመስጠት መርሐ ተካሂዷል።
በአድነው አሰፋ
የቢሮውን ተጨማሪ መረጃዎች ለማግኘት ![]()
በዌብሳይት https://www.cergcab.et/
በቴሌግራም https://t.me/CERGCAB
በፌስቡክ https://www.facebook.com/profile.php?id=100070605291100&mibextid=ZbWKwL
በቲውተር https://twitter.com/CabCerg2678
በቲክቶክ tiktok.com/@cerg2225


