
ሮተሪ ኢትዮጵያ የተመሰረተበትን 70ኛ ዓመቱን በብሔራዊ ቤተ-መንግስት አክብሯል።
በዝግጅቱም የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንትና የሮተሪ ኢትዮጵያ የበላይ ጠባቂ ታዬ አጽቀሥላሴ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፤ ሮተሪ ኢትዮጵያ ባለፉት 70 ዓመታት በጤና አገልግሎቶችና ሌሎች የልማት ዘርፎች ትርጉም ያለው ሥራ ሰርቷል።
የጤና አገልግሎት ጥራትና ደረጃን ለማሻሻል በተከናወኑ ተግባራትም ፖሊዮን ከኢትዮጵያ ለማጥፋት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱንም ተናግረዋል።
ሮተሪ ኢትዮጵያ ልዩ እሴቶች እና ቁርጠኝነት ያለው ተቋም ነው ያሉት ፕሬዝዳንት ታዬ፤ የፖሊዮ በሽታን ከኢትዮጵያ ለማጥፋት ላበረከተው ከፍተኛ አስተዋጽኦም አመስግነዋል።
የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ፤ ሮተሪ ኢትዮጵያ ፖሊዮን ከኢትዮጵያ በማጥፋትና በሌሎች የጤና ዘርፎች ላበረከተው ከፍተኛ አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል።
በቀጣይም ከሮተሪ ጋር ያለውን ትብብር በማጠናከር የጤና ሥርዓቱን ለማሻሻል በትኩረት እንደሚሰራ ተናግረዋል።
የሮተሪ ኢንተርናሽናል ፕሬዝዳንት ፍራንሲስኮ ኦሬዞ በበኩላቸው፤ ሮተሪ ኢንተርናሸናል በኢትዮጵያና ሌሎች ሀገራት ፖሊዮን የማጥፋት ዘመቻ ላይ በቢሊዮን ዶላር በላይ መድቦ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
በቀጣይም የኢትዮጵያን የጤና አገልግሎትና ደረጃ ለማሻሻል በሚደረገው ጥረት የበኩሉን ገንቢ ሚና ለመወጣት በቁርጠኝነት እንደሚሰራ አረጋግጠዋል።
በሌላ በኩልም ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ከሮተሪ ኢንተርናሽናል ፕሬዝዳንት ፍራንሲስኮ አሬዞን ጋር በጤና፣ በትምህርት፣ በሰላም ግንባታና ሌሎች ጉዳዮች ላይ በብሔራዊ ቤተ መንግሥት ተወያይተዋል።
Website: moh.gov.et
Facebook: Ministry of Health,Ethiopia
Twitter: x.com/fmohealth
YouTube: youtube.com/@FMoHealthEthiopia
Tiktok: tiktok.com/@mohethiopia
Telegram: t.me/M0H_EThiopia
Linkedin: lnkd.in/ewFJ6VAB




