
ባለፉት አመታት የእናቶችን ጤና ለማሻሻል ከህብረተሰቡ ጋር በመተባበር በፖሊሲ የተደገፉ ስራዎች ውጤት ማስገኘታቸውን የገለጹት ዶ/ር መቅደስ፤ በዚህም የእናቶች ሞትን በመቀነስ እ.ኤ.አ በ2000 ከነበረው 953 ከ100,000 የነበረዉን ሞት ወደ 195 ከ100,000 መቀነስ መቻሉን እና የጨቅላ ህፃናት ሞት ምጣኔን ከ 49 በ1000 በህይወት ከሚወለዱ ጨቅላ ህፃናት ወደ 26 ከ1000 በህይወት ከሚወለዱ ጨቅላ ህፃናት ዝቅ ማድረግ መቻሉን እና የወሊድ ክትትል እና በጤና ተቋም የመውለድ ምጣኔም በሰፊው መጨሩን ገልጸዋል፡፡ ጤና ሚኒሰቴር ይህንኑ ውጤት የበለጠ ለማሻሻል ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር አዳዲስ አሰራሮችን እና ፈጠራዎችን መተግበሩን እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡
ባለሙያዎች ለባለሙያዎች ስልጠና በመስጠት የእናቶች ጤና አገልግሎት ተደራሽነትን ማሳደግ መቻሉን የተናገሩት ዶ/ር መቅደስ፤ ፈጠራ እና ዘላቂ ፋይናንስን ተግባራዊ በማድረግ ጥራት ያለው የእናቶች ጤና አገልግሎትን ማሳደግ ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የሚጠበቅባቸውን ሃላፊነቶች እንዲወጡ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን፤ በሃገር ውስጥ የእናቶች እና ህጻናት መድሃኒቶችን እና የህክምና ቁሳቁስ ለማምረት ለጤና ተቋማት ድጋፍ እንደሚደረግ ሚኒስትሯ አክለዋል፡፡
በቀዶ ህክምና የወሊድ አግለግሎት የሚሰጡ ጤና ተቋማት ቁጥር እና አገልገሎት ሽፋንን መጨመር፣ ለእናቶች እና ጨቅላ ህፃናት አገልግሎት ዘላቂ የፋናንስ ምንጭ ማፈላለግ፣ እና ለእናቶችና ለጨቅላ ህጻናት ህክምና አገልግሎት የሚያስልጉ የግበዓቶችን አቅርቦት ማሻሻል ላይ በቀጣይ ትኩረት በመስጠት እንደሚሰራ የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ ገልጸዋል፡፡
የጤና ባለሙያዎች በየደረጃዉ ያለዉ አመራር፣ ሚድያ በለሙያዎችና ሁሉም ባለድርሻ አከላት የእናቶችና ህጻናት ጤናን በማሻሻል እንድሁም ሞትን ለመቀነስ በሚደረገዉ ርብርብ የድርሻቸዉን እንድወጡ ጥሪ ቀርቧል።
Website: moh.gov.et
Facebook: Ministry of Health,Ethiopia
Twitter: x.com/fmohealth
YouTube: youtube.com/@FMoHealthEthiopia
Tiktok: tiktok.com/@mohethiopia
Telegram: t.me/M0H_EThiopia
Linkedin: lnkd.in/ewFJ6VAB
