Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

የወራቤ ኮምፕርሄንሲቭ እስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የላቦራቶሪ ዳይሬክቶሬት በአምስት ዘርፎች እውቅና ተቸረው!

ሆስፒታሉ የአመቱ የሁለተኛ ሩብ አመት አፈጻጸም ላይ መክሯል።

በየዘርፉ ተለይቶ በቀረበ የየስራ ክፍሎች የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርትን መነሻ በማድረግ ነው ውይይት የተደረገው።

በተቋሙ ከጊዜ ወደ ጊዜ የታካሚዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ በሪፖርቱ ሲመላከት ህክምና ፈልገው ከሚመጡ ታካሚዎች ውስጥ የልብ በሽታ፣ አኒሚያ፣ የሳምባ ምች፣ ካንሰር የመሳሰሉት በብዛት ለህመም እና ሞት የሚዳርጉ በሽታዎች መሆናቸው በሪፖርቱ ተካቷል።

በተቋሙ በተሰራ ከፍተኛ የማስፋፊያ ስራ የሪፈር መጠንን ወደ ከአንድ በመቶ ለማድረስ ታቅዶ ወደ 0.5 በመቶ ዝቅ ማድረግ መቻሉም ተገልጿል።

በውይይቱ የሆስፒታሉ የማኔጅመንት አካላትን ጨምሮ ዳይሬክተሮች፣ የዘርፍ ኃላፊዎች እና የቡድን መሪዎች ተሳታፊ ሲሆኑ በቀረቡ የስራ አፈጻጸም ሪፖርቶች ላይ ሀሳብ አስተያየታቸውን አጋርተዋል።

በውይይት መድረኩ በመገኘት ግልጽነት በሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ በመስጠት የቀጣይ የስራ አቅጣጫ ያስቀመጡት የተቋሙ ዋና ስራ አስኪያጅ ዶ/ር ካሊድ ሸረፋ፣ ሜዲካል ዳይሬክተሩ ዶ/ር አብዲ ዋነንጎ፣ የጥራትና ፈጠራ ኮርፖሬት ዳይሬክተሩ ዶ/ር ሙሂዲን ዑመር እና የአስተዳደርና ልማት ኃላፊው አቶ ያሲን አወል ሲሆኑ በሩብ አመቱ የተሻለ አፈጻጸም መኖሩ መለየቱን ገልጸዋል።

በሩብ አመቱ በየዘርፉ በርካታ የተሻሉ የሚባሉ አፈጻጸሞች መመዝገባቸው ቢገለጽም ከታካሚ ቁጥር መጨመር ጋር ተያይዞ የጥራት ማሻሻያ ፕሮጀክቶችን/QI prject/ በመቅረጽ ሊፈቱ የሚገባቸው ጉዳዮች መኖራቸውም ተጠቁሟል።

አጋጠሙ የተባሉትን የህክምና ቁሳቁስ እና የስራ ቦታ እጥረት ቅደም ተከተል በመስጠት ለመፍታት ጥረቱ መቀጠሉን በማንሳትም የግዥ ሂደት ላይ የሚገኙ የህክምና መሳሪያዎች ገቢ ሲሆኑ መፍትሄ የሚያገኙ ጉዳዮች እንሚኖሩ ተገልጿል።

ባለአራት ወለል/G+3/ የሀኪሞች መኖሪያ ህጻም በአንጻራዊነት በቅርቡ እንደሚጠናቀቅ ያነሱት ዋና ስራ አስኪያጁ ዶ/ር ካሊድ ሸረፋ ከዚህ ጋር ተያይዞ ለአገልግሎት ማስፋፊያ የሚውል ክፍት ቦታ የሚገኝ መሆኑን አንስተዋል።

ተቋሙ ያነገበውን ራዕይ ለማሳካት ሁሌም ታትሮ እንደሚሰራ ያነሱት ዶ/ር ካሊድ ተቋሙ በቅርቡ በኢትዮጵያ የጥራት ድርጅት /Ethiopian Quality Award/ ተሸላሚ መሆኑ እና የላቦራቶሪ ዳይሬክቶሬት በአምስት ዘርፎች እውቅና ማግኘቱም የተሻለ ጥራት ያለው አገልግሎት ለመስጠት አጋዥ ነው ብለዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *