Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

የካራማራ አጠቃላይ ሆስፒታል የእናቶች እና የህጻናት ማዕከልን እና የሼክ ሃሰን ያባሬ ሆስፒታል ማዕከላዊ ላቦራቶሪ እንዲሁም የህጻናት እና የአዋቂዎች የድንገተኛ አደጋ ምርመራ ማዕከልን አስመርቀናል፡፡

በዛሬው ዕለት በሶማሌ ክልል በጅግጅጋ ከተማ በመገኘት ከሶማሌ ክልል ብሄራዊ መንግስት ፕሬዘዳንት ክቡር አቶ ሙስጠፌ መሃመድ ጋር በመሆን የጅግጅጋ ክልል ሪጅናል ላቦራቶሪን፤ የካራማራ አጠቃላይ ሆስፒታል የእናቶች እና የህጻናት ማዕከልን እና የሼክ ሃሰን ያባሬ ሆስፒታል ማዕከላዊ ላቦራቶሪ እንዲሁም የህጻናት እና የአዋቂዎች የድንገተኛ አደጋ ምርመራ ማዕከልን አስመርቀናል፡፡

በ300 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነባው የካራማራ አጠቃላይ ሆስፒታል የእናቶችና ህፃናት የጤና ማዕከል ከ100 በላይ የሚሆኑ አልጋዎች የያዘ ከመሆኑም ባሻገር የተጠናከረ እና ተገልጋይን መሰረት ያደረገ የጤና አገልግሎትን አሰጣጥን በማስፋፋት በክልሉ የእናቶች እና የህፃናት የጤና አገልግሎትን የሚያጠናክር ይሆናል፡፡

በመርሃግብሩ አብረን ያስመረቅነው የጅግጅጋ ክልል ሪጅናል ላቦራቶሪ ከዚህ ቀደም ከሚሰጠው መደበኛ የላቦራቶሪ ምርመራ አገልግሎት በተጨማሪ በተጠናከረ ሁኔታ አድቫንስድ የሞሎኪዩላር/ PCR ምርመራ፣ የህብረተሰብ ጤና አደጋዎች ሰርቪላንስ-ላቦራቶሪ፣ ማይክሮ ባዮሎጂ፣ ማይኮሎጂ ምረመራዎችን ለማካሄድ የሚያስችል ይሆናል፡፡

የሶማሌ ክልል ለዘርፉ እየሰጠ ላለው ከፍትኛ ትኩረት እንዲሁም ለተደረገልን መልካም አቀባበል የሶማሌ ክልል ብሄራዊ መንግስት ፕሬዘዳንት ክቡር አቶ ሙስጠፌን፤ የክልሉን አመራር፤ የጤና ባለሙያዎቻችን እንዲሁም ለሶማሌ ክልል ህዝብ ልባዊ ምስጋናዬን አቀርባለሁ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *