
የሆሳዕና ቅርንጫፍ ላብራቶሪ የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ አመት አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የነበሩ ጥንካሬዎች በቀጣይ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች በዝርዝር ተገምግሟል ፡፡
በክልሉ ጤና ቢሮ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ማሙሽ ሁሴን በአፈጻጸም ግምገማ መድረኩ እንዳሉት በግማሽ ዓመቱ የሆሳዕና ቅርንጫፍ ላብራቶሪ የላብራቶሪ አገልግሎቶችን በዙሪያው ላሉ ጤና ተቋማት በተሻለ መስጠት መቻሉን ገልጸዋል ፡፡
በተለይም የላብራቶሪ ናሙና ቅብብሎሽ ስርዓት ፣ የላብራቶሪ ጥራት ቁጥጥር ፣ የውጫዊ ቁጥጥር ስርዓት ላይ የተሰሩ ስራዎች ውጤታማ እንደነበሩ አስታውቀው በሁሉም ዘርፎች የተመዘገቡ አበረታች ውጤቶች ተጠናክረው መቀጠል እንደሚገባቸው አስታውቀዋል ፡፡
በቀጣይ ስድስት ወር ቅርንጫፍ ላብራቶሪው አገልግሎቶቹን በዙሪያው ያሉ በሁሉም ካችመንት ጤና ተቋማት ተደራሽ መሆን እንደሚገባ ገልጸው የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች በጊዜ እና በጥራት ማከናወን እንዲሁም በስሩ የሚገኙ ጤና ተቋማት የሰሩትን የላብራቶሪ ውጤቶች ማረጋገጥ ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባ ገልጸዋል ፡፡
በግማሽ ዓመቱ ቅርንጫፍ ላብራቶሪውን በግብዓት ለማሟላት ጥረቶች መደረጋቸውን ገልጸው በዛሬው ዕለትም ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚፈልጉ ናሙናዎች ማስቀመጫ ፍሪጅ እና ፈርኒቸር ርክክብ ተደርጓል ፡፡


