
የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና አንስቲትዩት የሕዝብ ግንኙነት እና ኮሚኒኬሽን ስራ አስፈፃሚ እና የቅድመ ማስጠንቀቂያ የሕብረተሰብ ጤና ስጋት ተግባቦት ዲቪዢን ከመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት እና ዩኒቨርስቲ በመጡ ምሁራን አማካኝነት ለኢንስቲትዩቱ አመራሮች የተሳካ የህዝብ ግንኙነትና የኮሙኒኬሽን ስራውች በሚል ርዕስ በአዳማ ከተማ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ እያካሄደ ይገኛል።
ዶ/ር ጌታቸው ቶሌራ የኢንስቲትዩቱ ም/ዋና ዳይሬክተር በስልጠናው ላይ እንደገለጹት ኢንስቲትዩቱ በምርምር፣ በሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች ቁጥጥር እና በላቦራቶሪ ዘርፎች በርካታ ስራዎች የሚሰራ እንደመሆኑ የተግባቦት (Communication) እና የሕዝብ ግንኙነት እነዚህን የሕብረተሰብ ጤና አገልግሎት ስራዎችን ለሕብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ ትልቅ አቅም መሆኑን ገልጸዋል።ኢንስቲትይቱ ለኮሙኒኬሽን ስራውች ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን የገለጹት ዶ/ር ጌታቸው የሚሰሩ የጥናትና ምርምር ስራውች የድንገተኛ የህብረተሰብ ጤና አደጋውች ላይ ሰፊ ግንዛቤ ለግብረተሰቡ ለመፍጠር እየተሰራም መሆኑን ትናግረዋል:: ኢንስቲትዩቱ ዋነኛ የጤና መረጃ አመንጪ እና ሀገራዊ የላብራቶሪ አቅሞችን እየገነባ ያለ መሆኑንም አስረድተዋል:: እነዚህ ትልልቅ ሀገራዊ ሀላፊነቶችም በሚጠበቀው ልክ መተዋወቅና ህብረተሰቡን ማሳታፍ እንደሚገባ አስረድተዋል::
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ጽ/ቤት ኃላፊ ዶ/ር አማር ባርባ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩ አስፈላጊነቱን አብራርተው ከአመራሩ የሚጠበቁትን ስራዎችም በዝርዝር ተናግረዋል። የልህቀት ማእከል መሆን ራእዩ የሆነው የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ግቦቹን ለማሳካት ከ ባለድርሻ አካላትና ከህብረተሰቡ ጋር በጠንካራ ግንኙነት እየሰራ መሆኑን ተናግረው እነዚህን ግኑኙነቶችን ከፍ ለማድረግና ታማኝነትን እና ተቀባይነትን ለማሳደግ ፈጣን እና ጥራት ያለው መረጃ መስጠት አስፈላጊነትን አስረድተዋል:: ለዚህ የህዝብ ግንኙነት ስራ መጠናከር ወሳኝ በመሆኑ በአመራሩ ትኩርት የተሰጠው ስራ መሆኑን ገልጸዋል::
የኢንስቲትዩቱ የሕዝብ ግንኙነት እና ኮሚኒኬሽን ስራ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ አለማየሁ ታረቀኝ ስለ ግንዛቤ ማስጨበጫው አላማ ሲያስረዱ ይህ በሁለት ዙር የሚሰጠው ስልጠና ኢንስቲትዩቱ የሚሰጠውን አገልግሎቶች እና መረጃዎች ለሕብረተሰቡ ብሎም ለሚመለከታቸው አካላት ተደራሽ ለማድረግ ለተቋሙ አመራሮች የህዝብ ግንኙነት እና ኮሙኒኬሽን ተግባር ለተቋማት ያለዉን ከፍተኛ ሚና አስመልክቶ ግንዛቤ በመፍጠር በጋራ በመስራት ውጤታማ የተደራሽነትና የተግባባት ስራዎችን ለማጠናከር ሲሆን በየደረጃው ያሉ የኢንስቲትዩቱ አመራሮች እና ከፍተኛ ባለሙያዎች በስልጠናው እየተሳተፉ ይገኛሉ በማለት አስረድተዋል።
አንዳንድ የመድረኩ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት ኢንስቲትዩቱ በርካታ ስራዎችን የሚሰራ እንደመሆኑ ከተለያዩ አጋር ድርጅቶችም ጋር የሚሰሩ በርካታ ፕሮጀክቶች ያሉ ሲሆን የነዚህን ስራዎች ውጤቶች ለሕብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ የተግባቦት ስራዎችን በጋራ እና አንዴትም መስራት እንዳለባቸው መገንዘባቸውን ገልጸዋል።
ስልጠናው ከመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት እና ከዩኒቨርስቲ በመጡ ምሁራን የተሰጠ ሲሆን የጤና ሚኒስቴር የኮሚኒኬሽን ባለሙያዎችም በዘርፉ ያላቸውን ተግባራዊ ልምድ አካፍለዋል።



