Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

ዘረመል መለየትን ጨምሮ የተለያዩ ዘመናዊ ምርመራዎችን እያከናወነ ያለው የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት

የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በከፍተኛ ወጪ ወደ ሀገር ባስገባቸው ዘመናዊ የሕክምና መሳሪያዎች ዘረመል መለየትን ጨምሮ የተለያዩ ዘመናዊ ምርመራዎችን እያከናወነ መሆኑን ገልጿል፡፡

ለ100 ዓመታት ሕብረተሰቡን ሲያገለግል የቆየው ኢንስቲትዩቱ፤ ራሱን በዘመናዊ ላብራቶሪ እና ቴክኖሌጂዎች በማደራጀት የበሽታን መነሻ ማወቅ የሚያስችሉ እና የተለያዩ የምርምር ሥራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ ከጤና ሚኔስቴር ጋር በመተባበር ባዘጋጀው የሚዲያ ፎረም ላይ ገልጿል፡፡

የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መሳይ ኃይሉ እንደገለጹት፤ ኢንስቲትዩቱ የሕብረተሰብ ጤና ማረጋገጥ እና በምርምር ሥራዎች ላይ በትኩረት እየሰራ ነው።

ተቋሙ በመንግሥት የተሰጠውን ኃላፊነት በአግባቡ በመፈጸም፣ የጤና ቁጥጥር እና ተደራሽነትን በማስፋት ለህብረተሰቡ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል ብለዋል።

እንደ ሀገር የሕብረተሰብ ጤና አዳጋዎች ወይም ወረርሽኝ በሚከሰትበት ወቅት የዳሰሳ ጥናት እና ምርምር በማድረግ ኢንስቲትዩቱ ፈጣን ምላሽ እንደሚሰጥ ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም ድንበር ተሻጋሪ የሆኑ ተላላፊ በሽታዎች ላይ ተገቢውን የቁጥጥር ሥራ እያከናወነ እንደሚገኝም ጠቅሰዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *