
ኢትዮጵያ በሁሉም ዘርፍ እያደረገች ባለችው ለውጥ በተለይም በመሰረተ-ልማት አቅርቦት፣ለቱሪዝም ምቹ በመሆን፣ለስብሰባ ምቹ የሆኑ አዳራሾችን እየገነባን እንዲሁም ለኢንቨስትመንት አመቺ የሆኑ ፖሊሲዎች እየተፈጠሩ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የመጣ እድል መሆኑን የገለጹት የጤና ሚኒስቴር ዴኤታ ወ/ሮ ፍሬህይወት አበበ ናቸው።
ሁለተኛው ኤግዚቢሽን በባለፈው ዓመት በጋና በተካሄደ ወቅት ሦስተኛውን የአፍሪካ የህክምና ግብዓት ምርት ኮንፍረንስ እና ኤግዚቢሽን ከብዙ ሃገሮች ጋር ተወዳድራ ኢትዮጵያ ካሏት ምቹ ሁኔታዎች አንፃር የተመረጠች መሆኑን የገለፁት ወ/ሮ ፍሬህይወት በኤግዚቢሽኑ ከስድስት መቶ በላይ ኢንቬስተሮች፣የፋይናንስ ተቋማት፣ተቆርቋሪዎች፣የፈጠራ እና የምርምር ባለሙያዎች እንዲሁም አምራቾች የሚሳተፉበት እንደሚሆን ገልጸዋል።
ወ/ሮ ፍሬህይወት አክለውም አፍሪካ እንደ አህጉር ሰባ በመቶ (70%) የሚሆነውን መድሀኒትና የህክምና ግብዓት ከተለያዩ አለም ሃገራት እንደምታስገባ ገልጸው በክትባት ረገድም አንድ በመቶውን (1%) ብቻ ነው በማምረት እየሸፈነች ያለው ብለዋል።
ኢትዮጵያ ይህንን ኤግዚቢሽን በማዘጋጀቷ የአፍሪካን የገበያ ድርሻ በተሻለ መልኩ ማግኘት ያስችላታል፣ ኢንቨስተሮችን ለመሳብ እንዲሁም በስፋት እየተሰራበት ያለውን ኢትዮጵያን የፋርመሲቱካል ሀብ የማድረግ ጥረት በብዙ መንገድ ያግዛል ብለዋል ወ/ሮ ፍሬህይወት።
በመጨረሻም ወ/ሮ ፍሬህይወት መገናኛ ብዙሃን ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት ኢትዮጵያ ያላትን ዘርፈ ብዙ መልካም አጋጣሚዎችን በስፋት ለዓለም የማሳወቅ ስራ እንዲሰሩ መልዕክት አስተላልፈዋል።
Website: moh.gov.et
Facebook: Ministry of Health,Ethiopia
Twitter: x.com/fmohealth
YouTube: youtube.com/@FMoHealthEthiopia
Tiktok: tiktok.com/@mohethiopia
Telegram: t.me/M0H_EThiopia
Linkedin: lnkd.in/ewFJ6VAB
