
የPEN-Plus ብሔራዊ የአሠራር ዕቅድ ማስጀመሪያ መርሀሃ-ግብር የተካሄደ ሲሆን፤ የSTEPS የዳሰሳ ጥናት ውጤቶች ይፋ ተደርገዋል፤ ይህም ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን (NCDs) ለመቀነስ ቁልፍ ምዕራፍ መሆኑ ተገልጿል።
በመክፈቻ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ እንደተናገሩት የሚቀጥሉት አምስት ዓመታት የመጀመሪያ ደረጃ የጤና እንክብካቤን ለማስፋፋት እና እየጨመረ የመጣውን ተላላፊ ያልሆኑ በሽዎችን ጫና ለመፍታት ወሳኝ ይሆናሉ። መንግሥት የጤና ስርዓቱን ለማጠናከር መረጃን፣ ዲጂታይዜሽን እና የሃገር ውስጥ ምርትን በማሳደግ ተላላፊ ያልሆኑ በሽዎችን ስርጭት ለመቀነስ ያለውን ቁርጠኝነት አፅንዖት ሰጥተዋል። ዶ/ር መቅደስ ተላላፊ ያልሆኑ በሽዎች ብሔራዊ ፈተና ብቻ ሳይሆን ዓለም አቀፍም መሆኑን በመጥቀስ ጠንካራ የኢንተር-ሴክቶራል ትብብር እንዲኖር ጥሪ አቅርበዋል።
የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጄ ዱጉማ የSTEPS ጥናት ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን ለመቀነስ በሚደረገው ጥረት በመረጃ ላይ የተመሠረተ ውሳኔ ለማድረግ ወሳኝ ማስረጃ ይሰጣል። ጥናቱ የሲጋራ እና የአልኮል ፍጆታ መቀነስን ቢያሳይም፣ ተላላፊ ያልሆኑ በሽዎች አሁንም እየጨመረ መሆኑን አብራርተዋል፣ ይህም የአኗኗር ዘይቤ ለውጦችን አስፈላጊነት አጉልተው ያሳያል ብለዋል።
የኢትዮጵያ የህዝብ ጤና ኢንስቲትዩት (EPHI) ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ጌታቸው ቶሌራ በዝግጅቱ ላይ ንግግር በማድረግ ውጤታማ የመከላከያ እና የቁጥጥር ስልቶችን በመቅረጽ ረገድ አስተማማኝ መረጃ አስፈላጊነትን አፅንዖት ሰጥተዋል።
PEN-Plus ዕቅድ ትገግበራ መጀመር እና የSTEPS የዳሰሳ ጥናት ውጤቶች ይፋ መሆን ኢትዮጵያ በመላ አገሪቱ የተላላፊ ያልሆኑ በሽዎችን ለመከላከል እና ለማስተዳደር በማስረጃ ላይ የተመሠረተ እርምጃ ለመውሰድ ያላትን ቁርጠኝነት ያሳያል።
Website: moh.gov.et
Facebook: Ministry of Health,Ethiopia
Twitter: x.com/fmohealth
YouTube: youtube.com/@FMoHealthEthiopia
Tiktok: tiktok.com/@mohethiopia
Telegram: t.me/M0H_EThiopia
Linkedin: lnkd.in/ewFJ6VAB



