Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

በአዮዲን እና ፎሊክ አሲድ የበለፀገ ጨው ላይ የተደረጉ የጥናትና የምርምር ግኝቶች ይፋ ተደረገ

የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ በመድረኩ የመክፈቻ ንግግራቸው እንዳሉት የጥናቶቹ ግኝት እናቶችን እና ህጻናትን ጤና ለመጠበቅ ይረዳል፣ እንደ የነርቭ ዘንግ ክፍተት ያሉ መከላከል የሚችሉ ጉዳቶችን በእጅጉ ለመቀነስ እንደሚረዳ ተናግረዋል።

የቅድመ ወሊድ ተጨማሪ ምግቦች ቢኖሩም፣ ለአብዛኛው ሴቶች አሁንም ተጨማሪ ስለሚያስፈልግ፣ ይህም የምግብ ማበልጸጊያን የበለጠ ሁሉን አቀፍ እና ዘላቂ መፍትሄ ያደርገዋል ብለዋል። ዶ/ር መቅደስ እንዳሉት ኢትዮጵያ በ2030 በሁሉም ቤተሰቦች ውስጥ አዮዲን እና ፎሊክ አሲድ የበለጸገ ጨው እንዲኖር ለማድረግ ያለመ ሲሆን ይህም በሰው ልጅ ካፒታል እና በሀገር አቀፍ ልማት ላይ የረጅም ጊዜ ኢንቨስትመንት እንደሆነ ገልጸዋል።

እንድስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል በበኩላቸዉ ይህ ፕሮጀክት የአኢትዮጵያ የዜጎችን ጤና በመጠበቅ ብልጽግናን የማረጋገጥ አካል መሆኑን በመግለጽ ጥናቱ በፎሊክ አሲድ እና አዮዲን የበለጸገ ጨው በሃገር ውስጥ ሊመረት፣ በማህበረሰቦች ተቀባይነት ሊኖረው እንደሚችል እና አሁን ያለውን የኢትዮጵያን የአዮዳይድ የጨው ስርዓት በመጠቀም የፎሊክ አሲድ መጠንን በብቃት እንደሚያሻሽል ተናግረዋል።

በአዮዲን እና ፎሊክ አሲድ የበለፀገ ጨው ላይ የተደረጉ የምርምር ግኝቶች ይፋ መደረጉ ንጥረ ነገሮችን እጥረት ለመፍታት እና የህዝብ ጤናን ለማሻሻል ትልቅ እርምጃ መሆኑን የተናገሩት የያዳም ፋውንዴሽን መስራች እና ሊቀመንበር፤ እና የቀድሞ የኢፊድሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስተር፤ አቶ ደመቀ መኮንን የተገኙ የጥናት ውጤቶችን መሰረት በማድረግ በፍጥነት ወደተግባር መግባት ያስፈልጋል ብለዋል።

Website: moh.gov.et

Facebook: Ministry of Health,Ethiopia

Twitter: x.com/fmohealth

YouTube: youtube.com/@FMoHealthEthiopia

Tiktok: tiktok.com/@mohethiopia

Telegram: t.me/M0H_EThiopia

Linkedin: lnkd.in/ewFJ6VAB

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *