Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

በተግዳሮቶች የማይበገር ዘላቂ የጤና ስርዓትን ለመገንባት የአቅም ግንባታ ስልጠና ወሳኝ መሆኑን የክልሉ ጤና ቢሮ ገለፀ

(ሆሳዕና፦ ጥር 4/2018) ”ጠንካራ የአመራር ግንባታ ለውጤታማ የጤና ስርዓት” በሚል መሪ ቃል የመጀመሪያ ዙር የጤናው ዘርፍ አመራር አቅም ማጎልበቻ ስልጠና በወራቤ ዩኒቨርሲቲ እየተሰጠ ነው።

በስልጠናው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ እንደተናገሩት ማህበራዊ ብልጽግናን በቤተሰብ ደረጃ ለማረጋገጥ የአመራር ስርዓቱን በስልጠና ማጠናከር ያስፈልጋል ብለዋል።

የጤናው ስርዓት ላይ ያጋጠሙ 15 ተግዳሮቶችን ለመፍታት የሚተገበሩ 12 ስትራቴጂክ መፍትሄዎች የተለዩ ሲሆኑ እነዚህም በአጭር፣ በመካከለኛ እና በረዥም ጊዜ የሚፈቱ ስለመሆናቸው ገልፀዋል።

የጤና ልማት ስራን ለማሳለጥ የአመራር እና የፈፃሚዎች ተነሳሽነት፣ተጠያቂነት እና ቁርጠኝነት ለጤናው ዘርፍ ወሳኝ በመሆኑ የዘርፉ መሪዎች ሚናቸውን በአግባቡ እንዲወጡ አሳስበዋል።

ለተሻለ ጤና አገልግሎት አሰጣጥ ጠንካራ አመራር አቅም ግንባታ ወሳኝ መሆኑን የገለፁት አቶ ሳሙኤል መሪነትን ባህል በማድረግ የጤናውን ስርዓትን ለማሻሻል በተደረገው ጥናት የመፍትሔ ሀሳቦች መቅረቡን ተናግረዋል።

ከወረቀት ነፃ የሆኑ የጤና አገልግሎት ለመስጠት የተጀመሩ የዲጂታል አገልግሎት አሰጣጥ ስርዓቱን በሁሉም መዋቅሮች ለማስፋፋት እየተሰራ ነው ብለዋል።

በመንግሥትና በህዝብ ተሳትፎ በጤና ተቋማት ግብአቶችን የማሟላት ተግባርን በማጠናከር የህዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተሰራ ነው ሲሉም ገልፀዋል።

በተለያዩ ተግዳሮቶች የማይበገሩ ዘላቂ የጤና ስርዓትን ለመገንባት የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች ወሳኝ ነው ያሉት አቶ ሳሙኤል ሰልጣኞ በቆይታቸው የሚያገኙት እውቀት ለችግሮች መፍትሔ የሚያበጁበትን ሂደት የሚያሳይ በመሆኑ ስልጠናው በጥብቅ ዲስፕሊን እንዲከታተሉ አሳስበዋል።

የወራቤ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኢንጂነር ቶፊቅ ጀማል በበኩላቸው በየጊዜው የሚሰጡ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች ለህብረተሰቡ እውቀት ላይ የተመሰረተ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል እንደሆነ ገልፀው

በዩኒቨርሲቲው በሚኖራቸው ቆይታ ለሰልጣኞች አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍና ክትትል እንደሚያደርጉም

ገልፀዋል።

በስልጠናውም የክልል፣ የዞን እና ልዩ ወረዳዎች የጤናው ሴክተር አስፈጻሚዎች እና ፈጻሚዎች የተገኙ ሲሆን ስልጠናውም ከዛሬ ጀምሮ እስከ ጥር 11/2018 ዓ.ም የሚሰጥና ቀጣይነት ያለው ስለመሆኑም ተገልጿል።

በአድነው አሰፋ

የቢሮውን ተጨማሪ መረጃዎች ለማግኘት ‼️

📌 በዌብሳይት https://www.cergcab.et/

📌በቴሌግራም https://t.me/CERGCAB

📌 በፌስቡክ https://www.facebook.com/profile.php?id=100070605291100&mibextid=ZbWKwL

📌 በቲውተር https://twitter.com/CabCerg2678

📌 በቲክቶክ tiktok.com/@cerg2225

📌 በዩቲዩብ https://youtube.com/@centralethiopiacommunication…

📌 በኢንስታግራም https://www.instagram.com/cergcab/profilecard/?igsh=MWNseXBlaW05dnM3MA==

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *