Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

በቀሪ ጊዜያት በእቅድ የተያዙ ተግባራትን ውጤታማ ለማድረግ በትብብር የመስራት ልምድ ማዳበር ይገባል :-ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰዉ (ዶ/ር)

(ታህሳስ 23/2018) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰዉ (ዶ/ር) ከወራቤ ክላስተር አመራሮች እና የማኔጅመንት አባላት ጋር በጽ/ቤታቸው ውይይት እያካሔዱ ነው

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰዉ (ዶ/ር)በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት በቀሪ ጊዜያት በእቅድ የተያዙ ተግባራትን ውጤታማ ለማድረግ በትብብር የመስራት ልምድ ማዳበር ይገባል ብለዋል።

በክልሉ በበጀት ዓመቱ የታቀዱ ስራዎች፣ያስገኙት ውጤት እንዲሁም ስራው የተመራበት መንገድ እና በቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ የጋራ ተግባቦት መፍጠር ይገባል ያሉ ሲሆን

ይህ የቅድመ 6 ወራት እቅድ አፈጻጸም ግምገማ በቀሪ ጊዜያት ለማከናወን የታቀዱ ስራዎችን በቅንጅት እና በትብብር ለመፈጸም እንደሚያግዝም ርዕሰ መስተዳድሩ አመላክተዋል።

አመራሩ ከሴክተሩ ግቦች በተጓዳኝ በዞኖች ያሉ ስራዎችን ማገዝ የሚያስችል ቅንጅታዊ አሰራር መዘርጋት ተገቢ ስለመሆኑም ርዕሰ መስተዳድሩ አብራርተዋል።

በመድረኩ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አንተነህ ፈቃዱን ጨምሮ የወራቤ ክላስተር አመራሮች እና የማኔጅመንት አባላት ተገኝተዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *