Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

ሃገር አቀፍ የጤና ቁጥጥር አድቮኬሲ ፎረም መካሄድ ጀመረ

የመጀመሪያው የጤና ቁጥጥር አድቮኬሲ ፎረም “ጠንካራ የጤና ቁጥጥር፤ ለማይበገር የጤና ስርአት!” በሚል መሪ ቃል መካሄድ ጀምሯል፡፡ ጤናማ እና ምርታማ ዜጋ ለመፍጠር ጠንካራ የጤና ቁጥጥር አስፈላጊነት ላይ አጽዕኖት በመስጠት የመድረኩን የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ፤ መድረኩ መዘጋጀቱ የጤና አገልግሎት ፈዋሽነትን የምናረጋግጥበት እና የህብረተሰቡን እምነት የምንገነባበት መድረክ ነው ብለዋል፡፡

የጤና ቁጥጥር የጤና ስርዓት ብቻ ሳይሆን የማይበገር ሃገር ለመፍጠር ይረዳል ያሉት ዶ/ር መቅደስ፤ ፎረሙ በጤና ቁጥጥር የደረስንበትን አቅም የምንገመግምበት መድረክ መሆኑን አስረድተዋል። የበሽታ ወረርሽኝን ለመቆጣጠር እና ለመከላከል የጤና ቁጥጥር አቅምን ማሳደግ ያስፈልጋል ብለዋል።

ከመከላከል ባለፈ አክሞ ማዳን ላይ ትኩረቱን ያደረገው አዲሱ የጤና አዋጅ ደህንነቱ የተጠበቀ የጤና አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑን ለማረጋገጥ እንደሚረዳ የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ፍሬህይወት አበበ የገለጹ ሲሆን፤ የጤና አገልግሎቱን ተደራሽ ለማድርግ ጥራቱን የጠበቀ አገልግሎት ለመስጠት የጤና አገልግሎት ምዘና እና ደረጃ መዘጋጀቱን አስረድተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ምግብ እና መድሃኒት ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ሄራን ገርባ በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ እየተሰሩ የሚገኙ የምግብ እና መድሃኒት ምርት ምዝገባ፣ የገበያ ፈቃድ፣ እና የቁጥጥር ስራዎችን ያብራሩ ሲሆን፤ የቁጥጥር ስርአታችንን እያጠናከርን ስንመጣ በሃገር ውስጥ የማምረት አቅማችንን እያሻሻልን እንመጠጣለን ብለዋል፡፡ ለዚህም ሃገራችን የማቹሪቲ ሌቭል ሶስት እውቅና ማግኘቷ የሃገራችን የመድሃኒት ምርት ተቀባይነትን ያሳደገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በአድቮከሲ መድረኩ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት፣ የጤና ቢሮ ሃላፊዎች እና ባለድርሻ አካላት የተሳተፉ ሲሆን፤ የጋራ የውይይት መድረክ አካሂደዋል፡፡

Website: moh.gov.et

Facebook: Ministry of Health,Ethiopia

Twitter: x.com/fmohealth

YouTube: youtube.com/@FMoHealthEthiopia

Tiktok: tiktok.com/@mohethiopia

Telegram: t.me/M0H_EThiopia

Linkedin: lnkd.in/ewFJ6VAB

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *