Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

በዱራሜ ከተማ አስተዳደር የወባ በሽታን ለመከላከል የአጎበር ስርጭት እየተካሄደ ይገኛል::

በከምባታ ዞን በዱራሜ ከተማ አስተዳደር የወባ በሽታን ለመከላከል የሚያስችል በኬሚካል የተነከረ የአልጋ አጎበር ስርጭት እየተካሄደ እንደሚገኝ ተገልጿል።

በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ሊከሰት የሚችለውን የወባ ወረርሽኝ ለመከላከል በኬሚካል የተነከረ የአልጋ የአጎበር ስርጭት በከተማ አስተዳደሩ በሚገኙ በአስሩም ቀጠናዎችና በሶስቱም ክፍለ ከተሞች በባለሙያዎች አማካኝነት እየተሰራጨ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ ጤና ጽ/ቤት አስታውቋል ።

የከተማ አስተዳደሩ ጤና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሀብትነህ ቲቶስ በከተማ አስተዳደሩ የሚስተዋለዉን የወባ በሽታ ሥርጭት ጫናን ለመግታት እየተካሄደ የሚገኘውን የወባ መከላከል ሥራን ለማጠናከር በመንግሥት አማካይነት የቀረበዉን የአልጋ አጎበር በከተማው የሚገኙትን የህብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራጨ መሆኑን ተናግረዋል።

ከአልጋ አጎበር አጠቃቀም በኩል የሚታዩ ጉድለቶችን ለመፍታት ለተጠቃሚዉ ህብረተሰብ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርቶችን መስጠት እንደሚያስፈልግ ገልፀው ህብረተሰቡ የሚሰራጨዉን አጎበር ለሌላ ተግባር ባለማዋል እና በአግባቡ በመጠቀም ራሱንና ቤተሰቡን ከወባ ህመምና ስቃይ ሊጠብቅ እንደሚገባ አቶ ሀብትነህ አሳስበዋል፡፡

ኃላፊዉ አክለዉም ከአልጋ አጎበር ስርጭት ጎን ለጎን የከተማዉን ህብረተሰብ በማስተባበር ለወባ ትንኝ መራቢያ አመቺ የሆኑ ያቆሩ ውሃዎችን የማፋሰስ፣ጉድጓዶችን የማዳፈን፣ የአካባቢ ጽዳት እና በወባ መከላከል ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ገልጸዋል።

የከምባታ ዞን ጤና መምሪያ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *