Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

በሀዲያ ዞን ጤና መምሪያ የ”40″ኛ ሣምንት “EOC” በመምሪያ ደረጃ ተገመገመ።

ሪፖርቱ በአቶ እንዳለ በኩል ሰፋ ባለ መልኩ የቀረበ ሆኖ ከወባ አንፃር የ40ኛ ሣምንት 1591 case ሆኖ ከአምናው ተመሳሳይ ሣምንት ከነበረው 1955 ቁጥር አንፃር የመቀነስ አዝማምያ ያለ ቢመስልም እንኳ ከባለፈው ሣምንት (39ኛ) አንፃር 1121 የነበረ ስለነበር 466 የጨመረበት ሁኔታ እንዳለ ተብራሮቷል።

‎ከፍተኛ የወባ ቁጥር የታየባቸው ሶሮ 169(10.6%), ጎምቦራ 150(9.4%), ሾኔ 144 ሆኖ ከወባ አይነት (species) አንፃር pf= 60% ሆኖ pv=38% mixed=2% እንደሆነ ተጠቅሶ pf መብዛቱ አሁንም የወረርሽኝ ስጋት መኖሩን የሚያሳይ እንደሆነ ተመልክቷል።

‎የምግብ እጥረት (SAM case) ጋር ተያይዞ በዝህ ሣምንት(40ኛ) ላይ 113 SAM case ሪፖርት የተደረገ እንደሆነና ከባለፈው ሣምንት (137) አንፃር መቀነስ የታየ ቢሆንም ከሪፖርት አደራረግ አንፃር ግን ሰፊ ጉድለቶች እንዳሉ ተጠቅሷል ለአብነትም SAM case ሪፖርት ተደርጎ MAM case 0 ብለው የላኩ ወረዳዎች አመካ,ምስራቅ ባደዋቾ,ፎንቆ,ጊቤ ወረዳ, ምሻ ወረዳና ሲራሮ ወረዳ መረጃቸውን መፈተሽ አለባቸው ተብሏል።

‎በመጨረሻም የመምሪያ ኃላፊ ዶ/ር ደሣለኝ ሹጉጤ ሲያጠቃልሉ የቀረበው ሪፖርቱም ሆነ ከቤቱ የቀረበው ሀሳብ ጥሩ እንደሆነ አንስተው የወባ በሽታ አሁንም አየጨመረ መሆኑን በደንብ መገንዘብ አለብን ብለዋል ምክንያቱም በትክክል ሪፖርት ከሁሉም አካል ቀርቦ ቢሆን ቁጥሩ ከዚህም ልበልጥ ስለምችል ሥራዎችን ተቀራርቦ መሥራት ያስፈልጋል ብለው በተለይም የመከላከሉን ሂደት ማለትም የአከባቢ ቁጥጥር ሥራችንን ከምንጊዜውም በላይ ማጠናከር ያስፈልጋል ብለዋል። ከመድሃኒት እጥረት ጋር ተያይዞ በተወሰነ መልኩ ለመፍታት የተሞከረ ስለሆነ ግብአቶችን ወረዳዎች በአግባቡ እንደመሩ አጽንዖት ሰጥተዋል። ከምግብ እጥረት ጋር ተያይዞ መረጃን አደራጅቶ መምራት እንደምያስፈልግ ጠቁመው የቀጣይ አቅጣጫዎችን ማለትም በየወረዳ RRTን ማጠናከር, የታመሙ ሰዎችን መፈለግ(strengthen Active search),task force ማጠናከር በሁሉም አከባቢ,አከባቢ ቁጥጥር ሥራን ማጠናከር, አጎበር አጠቃቀምን ማሻሻል እና ሪጭት በሚካሄድባቸው አከባቢዎች በጥብቅ ድስፕልን መምራት ያስፈልጋል ብለው የዕለቱ ስብሰባ ተጠናቋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *