Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

12ኛው አመታዊ የ COECSA ኮንግረስ ጉባኤ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ

“የተርሸሪ የአይን እንክብካቤን በ COECSA ሃገራት ማሳደግ፡ ጊዜው አሁን ነው” በሚል መሪ ቃል 12ኛው የምስራቅ፣ መካከለኛ እና ደቡብ አፍሪካ የዓይን ህክምና ኮሌጅ (COECSA) ኮንግረስ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል።

ኮንግረሱ አህጉራዊ እና አለምአቀፍ ባለሙያዎችን፣ የአይን ጤና ባለሙያዎችን እና ሰልጣኞችን ጨምሮ ከ40 በላይ ከሚሆኑ ሃገራት የተውጣጡ ከ600 በላይ ተሳታፊዎችን በማሰባሰብ በአፍሪካ የአይን ህክምናን ማሳደግ ላይ ምክክር ያደርጋል።

በመክፈቻ ንግግራቸው የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ COECSA ለኢትዮጵያ እና ለአካባቢው ሃገራት ያለውን ጠቀሜታ አጉልተዋል። በአፍሪካ የላቀ የአይን ህክምና መስጠት መጀመር ጊዜው አሁን ነው ያሉት ዶ/ር መቅደስ፤ የዘንድሮው መሪ ሃሳብ የተርሸሪ የአይን ህክምናን ለማስፋፋት ወቅታዊ እና አስቸኳይ መሆኑን አጽእኖት ሰጥተዋል።

ኢትዮጵያ የ2025 አመታዊ ጉባኤውን ከማዘጋጀት ባለፈ የኮሌጁን ፌሎሺፕ ፈተናዎችን በቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ ሆስፒታል እና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መስጠት ችላለች።

የCOECSA ኮንግረስ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ጆን ንክሮኪያ እንዳሉት በጉባኤው የአይን ጤና አገልግሎትን ለማጠናከር ተሳታፊዎቹ ውይይቶችን ያደረጋሉ፣ በተለያዩ አውደ ጥናቶች ይሳተፋሉ እንዲሁም የእውቀት መጋራት ላይ እንደሚሳተፉም ጠቁመዋል።

በእለቱ የኮሌጁ የ2025 ተመራቂዎች የምርቃት መርሃ-ግብር ተካሂዷል።

Website: moh.gov.et

Facebook: Ministry of Health,Ethiopia

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *