Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

የቻይና በጎ ፍቃደኛ የጤና ባለሙያዎች ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ተካሂዷል

የቻይና በጎ ፍቃደኛ የጤና ባለሙያዎች ማስጀመሪያ መርሃ ግብር በአዲስ አበባ ስልክሮድ ሆስፒታል ተካሂዷል።

የኢትዮጵያ እና ቻይና ወዳጅነት ውጤታማና ታሪካዊ መሆኑን የቻይና በጎ ፍቃደኛ የጤና ባለሙያዎች ማስጀመሪያ መርሃ ግብርን በይፋ የከፈቱት የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታየ አፅቀስላሴ ተናግረዋል።

ፕሬዚዳንት ታየ አክለውም የቻይና በጎ ፈቃደኛ ከፍተኛ የህክምና ባለሙያዎች ለበጎ ፍቃድ አገልግሎት ወደ ኢትዮጵያ መምጣታቸው የሁለቱ ሀገራት ወዳጅነት ጠንካራ መሆኑን ማሳያ ነው ብለዋል።

የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ በበኩላቸው በጤናው ዘርፍ በኢትዮጵያ እና በቻይና መካከል ያለው ትብብር ምሳሌ የሚሆንና ሊበረታታ የሚገባው መሆኑን ገልፀዋል።

የበጎ ፍቃደኛ የጤና ባለሙያዎች ልዑካን መምጣታቸው በጤናው ዘርፍ ለመስጠት የታቀደውን የበጎ ፍቃድ አገልግሎት እንደሚያግዝ ተናግረዋል።

የቻይና የህክምና በጎ ፍቃደኞች ከተመረጡ የሪፈራል ሆስፒታሎች ጋር በመተባበር በማህፀን ምርመራ እና ህክምና፣በአዕምሮ ህክምና፣በአይን እና በልብ ቀዶ ህክምና ዘርፎች አገልግሎት ይሰጣሉ።

Website: moh.gov.et

Facebook: Ministry of Health,Ethiopia

Twitter: x.com/fmohealth

YouTube: youtube.com/@FMoHealthEthiopia

Tiktok: tiktok.com/@mohethiopia

Telegram: t.me/M0H_EThiopia

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *