Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

የማእከላዊ ኢትዮጺያ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ስምምነት ፊርማ ስነ ስርዓት ተከናውኗል።

የክልሉ ህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ማሙሽ ሁሴን በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት ፈጻሚ ባለሙያን በሰራው የስራ አፈጻጸም ልክ ውጤቱን ለመለካት የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል።

የውል ስምምነቱ የሆሳዕና ቅርንጫፍ ላቦራቶሪን ጨምሮ ተቋሙ ላይ ካሉ የድንገተኛ አደጋዎች እና ወረርሽኞች ቁጥጥር : የህብረተሰብ ጤና ላቦራቶሪ እንዲሁም የጥናት እና ምርምር ዘርፎች ጋር የተደረገ ነው።

በቀጣዩ ዓመት የላቀ የጤና ጤና ነክ ድንገተኛ አደጋዎች የአሰራር ስርዓቱን ወደላቀ ደረጃ ለማድረስ ሁሉም የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ ይገባል ብለዋል።

የክልሉን የህብረተሰብ ጤና ላብራቶሪ ጥራቱ የተጠበቀ የላቀ የላብራቶሪ አገልግሎት እንዲሰጥ የሚያስችል ስራ ለመስራት ርብርብ ማድረግ እንደሚገባ አመላክተዋል።

የጥናትና ምርምር ስራዎች ላይ የነበሩ ቅንጅታዊ አሰራሮች የመጡትን ውጤቶች አስጠብቆ ማስቀጠል ይገባልም ብለዋል።

በ2017 በጀት ዓመት የነበሩ ጠንካራ አፈጻጸሞችን አስጠብቆ ከማስቀጠል እና በ2018 በጀት ዓ.ም የላቀ ደረጃ ላይ ለማድረስ ሁሉም የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት አቶ ማሙሽ ጠይቀዋል።

በመጨረሻም ከሚመለከታቸው የስራ ኃላፊዎች ጋር የዕቅድ ስምምነት ፊርማ ስነ ስርዓት ተካሂዷል።

በዝናሽ ደለለኝ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *