
ነሀሴ 15/2017
የሀላባ ዞን ጤና መምሪያ የ2018 በጀት አመት የመጀመሪያ ወር አፈጻጸም እና ሳምንታዊ የEOC ግምገማ በዛሬው እለት ተካሂዷል፡፡
የአፈጻጸም ሪፖርቱ በልማት እቅድ ቡድን መሪ አቶ ሀብታሙ ጽጌ የቀረበ ሲሆን ሳምንታዊ የEOC ሪፖርት በድንገተኛ በሽታዎች አሰሳ እና ቅኝት ቡድን መሪ በሆኑት በአቶ ነስረዲን ኑርዬ አማካኝነት ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጓል፡፡
በግምገማ መድረክ የመምሪያው ኃላፊ ዶ/ር ሸምሱ ረሺድ እንደገለጹት በበጀት አመቱ እየተከናወኑ ያሉት ተግባራት እየገመገምን ከመራን እና የነበሩብንን የአፈጻጸም እንዲሁም የመረጃ ጥራት ችግሮችን እየለየን በትኩረት ከሰራን የተሸለ አፈጻጸም እና የህዝብ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ እንደሚቻል ገልጸዋል፡፡
ዶ/ር ሸምሱ አክለው ለጤና አፈጻጸም መሰረት የሚሆነው ከወረዳዎች እና ከጤና ተቋማት ሪፖርት ተሟልቶ እና በወቅቱ በDHIS2 ሲተላለፍ እንደሆነ ገልጸው ሁሉም መዋቅር በተቀመጠለት የጊዜ ገደብ የመረጃ ጥራቱን ፈትሾ ሪፖርቱን መላክ እንዳለበት ያሰሰገነዘቡ ሲሆን የ2018 የመጀመሪያ ወር አፈፃፀም በመዋቅሮች እና በዞን ደረጃ በእናቶች እና ህጻናት፣ በበሽታ መከላከል እና ቁጥጥር ስራዎች እና ተላላፊ ያለሆኑ በሽታዎች ልየታ እና ህክምና ላይ አመርቂ ውጤቶች መመዝገባቸውን ገልጸዋል፡፡
በተጨማሪም የወባ መከላከል ተግባራት፣በማህበረሰብ ቲቢ ልየታ፣የኤች አይ ቪ መከላከል እና ምርመራ፣የህሙማን ቅብብሎሽ ስርአት እና የህጻናት ክትባት አገልግሎት አፈጻጸምን ለማሻሻል በትኩረት መሰራት እንዳለበት የገለጹ ሲሆን በወረዳ እና በጤና ተቋማት የአፈጻጸም ገምጋሚ ቡድን፣የፈጣን ምላሽ ሰጪ ቡድን እና የማኔጅመንት ውይይቶች ችግር ፈቺ በሆነ መልኩ ወቅቱን ጠብቀው ውይይት መደረግ እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡
በመጨረሻም የመድረኩ ተሳታፊዎች በቀረበው ሪፖርት ላይ ሀሳብ አስተያየት በመስጠት እና በቀጣይ ተግባራት ላይ በቁርጠኝነት ለመተግበር ከስምምነት በመድረስ የእለቱ ግምገማ ተጠናቋል፡፡
የአፈፃፀም መድረኩ ላይ የመምሪያው ኃላፊ፣ የመምሪያው ማኔጅመንት አባላት፣ የወረዳ ጽ/ቤት ኃላፊዎች እና የልማት እቅድ አስተባባሪዎች በተገኙበት በጋራ ተገምግሟል፡፡




