Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

ከ15 የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ የፊልድ ኢፒዲሞሎጂ ሬዝደንት አማካሪዎች ቴክኖሎጂ በትምህርት ስርዓቱ ስለሚካተትበት ሁኔታ እየመከሩ ነው

ከ15 የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ የፊልድ ኢፒዲሞሎጂ ሬዝደንት አማካሪዎች በአፍሪካ የህብረተሰብ ጤና ችግሮችን በፍጥነት ለመለየት፣ ለመመርመርና ለማከም እንዲቻል ዘመን ያፈራው ቴክኖሎጂ በትምህርት ስርዓቱ በሚካተትበት ሁኔታ በአዲስ አበባ እየመከሩ ነው።

የፊልድ ኢፒዲሞሎጅ ስልጠና ፕሮግራም ለህብረተሰብ ጤና አገልግሎት የጀርባ አጥንት መሆኑን የገለፁት የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሳህረላ አብዱላሂ ቀጣዩ የአፍሪካ ጤና አገልግሎት በመረጃ ላይ የተመሰረተ እንደመሆኑ የኢፒዲሞሎጅ ባለሙያዎች በቴክኖሎጅ በመታገዝ ወረርሽኞችን ለመቆጣጠር ብቻ ሳይሆን ቀድሞ ለመተንበይና ለመከላከል ያስችላቸዋል ብለዋል፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት በሁሉም ደረጃ ለመተግበር ቁርጠኛ መሆኗንም ገልፀዋል፡፡

የኔትዎርኩ አላማ በአፍሪካ የሚሰሩ የኢፒዲሞሎጅ ባለሙያዎችን አቅም በቴክኖሎጅ መገንባት መሆኑን የገለፁት የአፍሪካ ፊልድ ኢፒዲሞሎጂ ኔትወርክ / አፊኔት/ አባል ዶ/ር ገብረክርስቶስ ነጋሽ በበኩላቸው ትግበራው ሲጀመር የኢፒዲሞሎጅ ባለሙያዎች መረጃዎችን የመተንተን የህብረተሰብ ጤና ችግሮችን በፍጥነት የመለየት፣ የመከላከልና የመቆጣጠር አቅማቸውን እንደሚያሳድግላቸው ገልፀዋል፡፡

የኢፒዲሞሎጅ ስልጠና ፕሮግራም በ3 ወር – ፍሮንት ላይነር፣ በ9 ወር – ኢንተርሚዲየት እና በ2 ዓመት – አድቫንስድ ደረጃዎች የሚሰጥ የስልጠና ፕሮግራም ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *