Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

ትክክለኛ እና የተደራጀ የጤና መረጃ ስርዓትን በማጠናከር በህብረተሰቡ ላይ ሊክሰቱ የሚችሉ የጤና ስጋቶችን ቀድመን መከላከል እንደሚገባ የክልሉ ጤና ቢሮ አስታወቀ

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ የህብረተሰብ ጤና እንስቲትዩት የድንገተኛ አደጋዎች ቅኝትና ምላሽ ዳይሬክቶሬት ከዞንና ከልዩ ወረዳ ለተውጣጡ የአደጋ ስጋት ግንኙነት እና የማህበረሰብ ተሳትፎ ተጠሪዎች (RCCE) ጋር የዉይይት መድረክ አካሂዷል ።

በኢንስቲትዩቱ የጤናና ጤና ነክ ድንገተኛ አደጋዎች ቅኝትና ምላሽ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ወልደሰንበት ሸዋለም በዚህ ወቅት እንደተናገሩት ትክክለኛና የተደራጀ የጤና መረጃ ስርዓትን በማጠናክር በህብረተሰቡ ላይ ሊከሰቱ የሚችሉ የድንገተኛ የጤና አደጋ ስጋቶችን ቀድመን መከላከል ይገባል ብለዋል።

ጥራቱን የጠበቀ የጤና መረጃ ለዜጎች ተደራሽ ማድረግ ፋይዳው የጎላ ነው ያሉት ዳይሬክተሩ የመረጃ ስርዓታችንን በማጠናክር የህብረተሰቡን ችግር ሊቀርፍ በሚችል መልኩ በማዘመን የጤና አገልግሎቱን በተገቢዉ መስጠት እንደሚገባ አመላክተዋል።

በክልሉ የወባ በሽታ ጫናው በፊት ከነበረበት የመቀነስ ነገር ቢታይም ችግሩን በዘላቂነት ለመቅረፍ የተሟላና ያልተቆራረጠ መረጃዎችን ለህብረተሰቡ ተደራሽ በማድረግ የዜጎችን ተሳትፎና ንቃተ ጤና ማሳደግ ተገቢ ስለመሆኑም አቶ ወልደሰንበት አንስተዋል ።

በክልሉ የክረምት ወቅትን ተከትሎ ሊከሰቱ የሚችሉ የወባ በሽታን ጨምሮ ሌሎች የድንገተኛ አደጋዎችን ቀድመን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን በማስፋት እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተገቢው ሰዓት ለማድረስ ቁርጠኛ መሆን ይግባል።

እንደ አቶ ወልደሰንበት ገለፃ በመረጃ ላይ የተደገፈ ስርዓትን ተግባራዊ ለማድረግ እስከ ታች መዋቅር ድረስ በመዝለቅ የህብረተሰቡን እምነት፣ የመረጃ አጠቃቀም ፣ክህሎት፣አመለካከት እና መሠል ችግሮችን ለመቅረፍ መረጃን በጥራት እና በተጠያቂነት ለማድረስ የዘርፉ ባለሙያዎች ላይ በትኩረት መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል።

የጤና ቢሮ ህዝብ ግንኙነት እና ጤና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ቢኒያም ገዙ የተለያዩ የሚዲያ አማራጮችን በመጠቀም ትክክለኛ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለህብረተሰቡ ተደራሽ በማድረግ ከጤና ስጋቶች እንዲጠበቅ ይሰራል ብለዋል ፡፡

የክልሉ ህብረተሰብ በቂ የጤና አደጋዎች ስጋት መረጃዎች እንዲኖሩት ከጤናና ጤና ነክ ድንገተኛ አደጋዎች ቅኝትና ምላሽ ዳይሬክቶሬት ጋር በቅንጅት የተዘጋጀ መድረክ መሆኑን ገልጸው ቢሮው ከሁሉም የስራ ክፍሎች ጋር በመቀናጀት ለሚዲያ እና ኮሚኒኬሽን ባለሙያዎችን በጤና መረጃዎች ላይ የአቅም የመገንባት ስራዎችን አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል ፡፡

የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው በቀጣይ ትክክለኛ መረጃን ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ እና የተለያዩ የሚዲያ አማራጮችን በመጠቀም የማህበረሰቡን ችግር ሊቀርፍ በሚችል መልኩ ለመስራት ቁርጠኛ መሆናቸውን ጠቁመዋል

በሸምሲያ አደም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *