Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

በጤናው ዘርፍ ትርጉም ያለው ለውጥ እንዲመዘገብ የአለም ጤና ድርጅት እያደረገ ያለው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው-ዶ/ር መቅደስ ዳባ

___________

በቅርቡ በአፍሪካ የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ሆነው የተሰየሙት ፕሮፌሰር መሃመድ ያኩብ ጃናቢ የተመራ ልዑክ ከጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ጋር በቀጠናዊ እና ሀገራዊ የጤናው ዘርፍ ትብብርና ትግበራ ዙሪያ ውይይት አደርጓል።

በጤናው ዘርፍ ትርጉም ያለው ለውጥ እንዲመዘገብ የአለም ጤና ድርጅት እያደረገ ያለው አስተዋጽኦ ከፍተኛ እንደሆነ የገለጹት የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ በተለይ ሁሉን አቀፍ የጤና ሽፋንን እውን ለማድረግ እየተደረገ ያለዉ ጥረት ተጠናክረዉ መቀጠል አለበት ብለዋል። የማህበራዊ ጤና መድህን፣ የመጀመሪያ ደረጃ ጤና ክብካቤ፣ የድንገተኛ የጤና አደጋ እና ወረርሽኝን ከመከላከልና መቆጣጠር አንፃር እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን ከመደገፍ ረገድ ተቋሙ ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጎን እንዲቆም ሚኒስትሯ ጠይቀዋል።

እንደ ሀገር የዜጎችን ጤና ከማስጠበቅ አኳይ እንዲሁም በጤናው ዘርፍ የመጡ ለውጦች አበረታች መሆናቸውን የገለጹት በአፍሪካ የአለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ፕሮፌሰር መሃመድ ያኩብ ጃናቢ በበኩላቸዉ የሀገር ውስጥ ምርትና ከሀገራት ጋር በትብብር መስራት፣ የበሽታ ቅኝትና ቁጥጥርን ማጠናከር፣ የጤና መድኃን ፕሮግራምን ማስፋፋት፣ የግሉ የጤና ዘርፍን ማበረታታት እና የሀገር ውስጥ የሀብት አሰባሰብና አጠቃቀምን የማሻሻል ስራዎችን አጠናክሮ መስራት እንደሚገባ ጠቅሰው ለዚህም የዓለም ጤና ድርጅት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልጸዋል።

Website: moh.gov.et

Facebook: Ministry of Health,Ethiopia

Twitter: x.com/fmohealth

YouTube: youtube.com/@FMoHealthEthiopia

Tiktok: tiktok.com/@mohethiopia

Telegram: t.me/M0H_EThiopia

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *