
የማዕከላዋ ኢትዮጵያ ክልል የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ሳምንታዊ የሕብረተሰብ ጤና ድንገተኛ አደጋዎች ማስተባበሪያ ማዕከል(Public health EOC) ግምገማ በዛሬው ዕለት አካሂዷል ።
ሳምንታዊ የበሽታዎች ቅኝትና የምላሽ ስራዎች ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጓል።
በውይይቱም በትኩረት ከተነሱ ነጥቦች፤ወባን ጨምሮ ሳምንታዊ የሕብረተሰብ ጤና ድንገተኛ አደጋዎች ቁጥጥር ፤ተግባራት አፈጻጸም በዝርዝር የተገመገመ ሰሆን፤ የመፍትሔ አቅጣጫና የድርጊት መርሐግብር ተቀምጧል።
በተፈጥሯዊ እና ሰው ሰራሽ በሆኑ አደጋዎች ምክንያት የሚከሰቱ የህብረተሰብ ጤና አደጋዎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ተመላክቷል፡፡
የወባ በሽታ ስርጭትን ለመቆጣጠር ሁለንም ዓይነት የመከላከል እና የመቆጣጠር ተግባራትን አቀናጅቶ ማከናወንና በቅርበት መገምገም እንዳለበት የውይይት መድረኩ አጽንኦት ሰጥቶ መክሮበታል ።
በተጨማሪም አሁን ላይ ያለውን የወባ ስርጭት ለመቆጣጠር በሁሉም የክልሉ አከባቢዎች ላይ የቅርብ ክትትል ማድረግ፤ ቤት ለቤት የተሰራጨውን አጎበር አጠቃቀም መከታተል የማህበረሰብ ግንዛቤ ማስጨበጫ እና የንቅናቄ ስራዎችን በልዩ ትኩረት መፈጸም አንዳለበት ተጠቁሟል።
በዝናሽ ደለለኝ

