Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ በወልቂጤ ዩኒቨርስቲ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የካንሰር ህክምና መስጫ ማዕከል መርቆ ከፈተ።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ በወልቂጤ ዩኒቨርስቲ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የካንሰር ህክምና መስጫ ማዕከል መርቆ ከፈተ።

የቢሮው ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በሆስፒታሉ ተገኝተው የማዕከሉን ሥራ በይፋ አስጀምረዋል።

ማኔጅመንቱ በሆስፒታሉ እየተሰጡ የሚገኙ የህክምና አገልግሎቶችን ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን፣ የህብረተሰቡን ጤና ለማሻሻል በተቋሙ የተጀመሩ ሥራዎች ተስፋ ሰጪ መሆናቸውን ተመልክቷል።

የሆስፒታሉ ስራ-አስኪያጅ ዶ/ር ፍቅረ-ጽዮን በዚህ ጊዜ እንደተናገሩት፦ ሆስፒታሉ ወደ ሥራ ከገባ 5 ዓመት ቢሆነውም የህብረተሰቡን ጤና ተደራሽነት ለማረጋገጥ ዘርፈ ብዙ ተግባራት እየተከናወኑ ነው።

በዚህ ጊዜ የ2017 የክረምት ወራት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ማስጀመሪያ ፕሮግራም ተካሂዷል።

በወቅቱም፦ አረንጓዴ አሻራ ማኖር፣ የደም ልገሳና ነጻ የጤና ምርመራ መርሃ-ግብሮች ተደርገው የዘንድሮው በጤና ዘርፍ የሚደረገው የክረምት ወራት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ወደ ተግባር ተገብቷል።

በ2016 የክረምት ወራት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ጤና ተቋማት የእውቅና ሰርትፍኬት ተሰጥቷቸዋል።

አብርሃም ሙጎሮ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *