
በ27ተኛ ሳምንት 7ሺህ 77ሰዎች የወባ ምርመራ ከተደረገላቸዉ መካከል 1 ሺህ 6መቶ 58 ሰዎች በወባ ሲያዙ የ10 ሰዎች ተኝተው ታክመዋል፡፡ በዞኑ ያለው የወባ መገኘት ምጣኔ 23 በመቶሲሆን ፕላዝሞዲየም ፋልሲፈረም 754(46%)፣ፕላዝሞዲየም ቫይቫክስ 885(54%) መሆኑን መረጃዎች ያመላክታሉ።
በሳምንቱ በከፍተኛ ሁኔታ የጨመረባቸው መዋቅሮችአለም ገቢያ 269፣ ዳሎቻ ከተማ 206 ፣ ሳንኩራ ወረዳ 189 ፣ ምስራቅስልጢ ወረዳ 171 ፣ሁልባራግ ወረዳ 161 ጦራ ከተማ 102 በመያዝ የዞኑን የወባ ጫና የሚሸፍኑ ናቸወ።
የጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ሸምሱ ሀይረዲን እንዳነሱት በሳምንቱ የወባ ሕሙማን ቁጥር ካለፈው ሣምንት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ3 .5 በመቶ ቅናሽ ማሳየቱን ተጠቁሟል፡፡ ያለንበት የክረምን ወቅት እንደመሆኑ የዝናብ መቆራረጥ ለችግሩ መባባስ ከፍተኛ ድርሻ የሚወስድ ሲሆን የአካባቢዉ ቁጥጥር ስራ በበቂ ሁኔታ አለመሰራቱ ማሳያ ነዉ፣የአልጋ አጎበር በአግባቡ አለመጠቀም በእጃችን ያሉ የወባ በሽታ መከላከያዎች ሲሆኑ።
ቤት ለቤት ጉብኝት የጤና ኤክስቴንሸን ሰራተኞችን በመደገፍ ታቅዶ መስራት ያስፈልጋል ፣ በእምነት ተቋማቶች፣ በመሰብሰቢያ ቦታዎች የወባ በሽታ መከላከል እና መቆጣጠር ሂደት ላይ ውይይት በማድረግ እና ውሃ ያቆሩ ስፍራዎችን የማዳፈን፣ የአልጋ አጎበሮችን በአግባቡ የመጠቀም ልምዶችን በማሳደግ የወረርሽኝ በሽታዉን መከላከልና መቆጣጠር ይቻላል፡፡
የስልጤ ዞን ጤና መምሪያ
ነሀሴ 4/2017 ዓ/ም


