
የከምባታ ዞን ጤና መምሪያ የድንገተኛ አደጋዎች ኦፕሬሽን ማዕከል (EOC) ሳምንታዊ ግምገማ አካሄደ
**************
ሀምሌ 3/2017 ዓ.ም የከምባታ ዞን ጤና መምሪያ የድንገተኛ አደጋዎች ኦፕሬሽን ማዕከል (EOC) ለህብረተሰቡ ጤና ስጋት ሊሆኑ የሚችሉ የጤናና ጤና ነክ ክስተቶች ቅኝትና ምላሽ ተግባራት ዙሪያ ሳምንታዊ ግምገማ አካሂዷል።
በመድረኩ የክረምት መግቢያን ተከትሎ የሚስተዋለው የአየር ሁኔታ ለወባ ትንኝ መራቢያ ምቹ ሁኔታ የሚፈጥር በመሆኑ አስቀድሞ በሽታውን ለመከላከል በየደረጃው ሊሰሩ በሚገቡ የቅኝትና ምላሽ ተግባራት ዙረያ በቀጣይ ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች በሚመለከት ዉይይት ተደርጓል።
የዉይይት መድረኩን የመሩት የዞኑ ጤና መምሪያ ኃላፊ ዶ/ር ራመቶ አቦ የክረምት መግቢያን ተከትሎ በመጨመር ላይ የሚገኘዉን የወባ በሽታ ስርጭትን ለመግታት የወባ መከላከል እና የቁጥጥር ስራዎች ላይ የወባ በሽታ ቅኝትና ምላሽ ተግባራት፣የወባ ምርመራ እና ህክምና አገልግሎትን አጠናክሮ መስጠት እና ሌሎችም የመከላከል ተግባራት ከወዲሁ በየደረጃው ልዩ ትኩረት በመስጠት ሊተገበሩ እንደሚገባ አሳስበዋል።
በመጨረሻም በቀጣይም ለህብረተሰቡ ጤና ስጋት ሊሆኑ በሚችሉ የጤናና ጤና ነክ ክስተቶችን ለመከላከል የድርጊት መርሃ ግብር ተዘጋጅቶላቸው በቀጣይ የሚሰሩ ተግባራት ዙሪያ የጋራ መግባባት ተፈጥሮ ዉይይቱ ተጠናቋል።