Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

ለሶስት ተከታታይ ቀናት የህብረተሰብ ጤና መረጃ አያያዝ እና ትንተና ላይ ያተኮረው የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ተጠናቀቀ ፡፡

ለተከታታይ ሶስት ቀናት በቡታጅራ ከተማ ሲሰጥ የነበረው የStat እና R ሶፍትዌር ስልጠና መጠናቀቁን የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህ/ሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቋል

በስልጠናው ላይ የክልሉ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምርምር ተቋም ባለሙያዎች፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከጤና ቢሮ፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከሉ ዩንቨርስቲዎች፣ ኮሌጅዎች ፣ ከዞን እና ልዩ ወረዳ ባለሙያዎች የተሳተፉ ሲሆን ተሳታፊዎቹ ከስልጠና መጨረሻ ላይ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ደይሬክተር ከሆኑት ከአቶ ማሙሽ ሁሴን ጋር ባደረጉት ውይይት ስልጠናው መረጃን ለዉሳኔ ለመጠቀም Evidence synthesis ለማድረግ እጅግ አስፈላጊ መሆኑን ያስቀመጡ ሲሆን፤ በቀጣይ ስልጠናው በጤና ቢሮ እና በምርምር ተቋማት ደረጃ ለሚገኙ ባለሙያዎች ቢሰጥ መረጃዎችን ለውሳኔ ለመጠቀም የሚኖረው ሚና የጎላ መሆኑን በዉይይቱ ላይ አንስተዋል ።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ደይሬክተር አቶ ማሙሽ ሁሴን ስለተሰጠው ስልጠና የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና የኢንስቲትዩትን አመስግነው በቀጣይም ተመሳሳይ ስልጠና እንደ አስፈለጊነት በየደረጃ የሚሰጥ መሆኑን ተነግሯል።

ሰልጣኞች በሰለጠናው ወቅት የወሰዱትን እውቀት ወደ ትግበራ በመቀየር ለህብረተሰቡ ጠቃሚ መረጃ በመወጣት ለዉሳኔ ሰጭዎች ድግፍ እንድያደርጉ ጠይቀዋል ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *