
በክልሉ በተፈጥሮ ከመጠን በላይ የፈሳሽ ክምችት እና የነርቭ ዘንግ ክፍተት ተጠቂ የሆኑ ህጻናት ህክምና እና ድጋፍ እንዲያገኙ የሚያስችል ስምምነት መሆኑ ተገልጿል ፡፡
ስምምነቱን በማስመልከት ንግግር ያደረጉት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ በክልሉ በተፈጥሮ የጤና ችግር ያለባቸው ህጻናት ፈጣን ህክምና እንዲያገኙ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል ፡፡
በተለይም በተፈጥሮ የከንፈር እና ላንቃ መሰንጠቅ ፣ ሲወለዱ ቆልማማ እግር የሆነ ፣ የኦቲዝም ችግር ያለባቸው ህጻናት ህክምና እና እንክብካቤ እየተደረገ መሆኑን አንስተው በክልሉ በዚህ ችግር ያለባቸው ህጻናት ቁጥር ከሚታሰበው ከፍ ያለ መሆኑን ገልጸዋል ፡፡
በክልሉ አብሮ ለመስራት ዝግጁ የሆነ ቅን የሆነ የመንግስት አመራር እንዳለ ገልጸው ይህ በተፈጥሮ የተከሰቱ የጤና ችግር ያለባቸው ህጻናት ህክምና አገልግሎት የሚሰራው የመንግስት ኃላፊነት ስለሆነ ብቻ አለመሆኑን ገልጸው ሰብዓዊ ግዴታችን ጭምር በመሆኑ የሚሰራ ነው ብለዋል ፡፡
በክልሉ ወራቤ ኮንፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታልን ጨምሮ በሌሎቹም ሆስፒታሎች ህክምና ከድርጅቱ ጋር ለመስራት ሁሉም ሆስፒታሎች በጋራ ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠው የክልሉ ጤና ቢሮ በሚችለው አቅም ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል ፡፡
hope shb ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ወ/ሮ ቤዛ በሻ በበኩላቸው የማዕከላዊ ኢትዮጽያ ክልል ከእኛ ጋር አብሮ ለመስራት የወሰደው ተነሳሽነት ለሌሎች የኢትዮጽያ ክፍሎች አርአያ የሚሆን መሆኑን አንስተዋል ፡፡
የክልሉ የጤናው ዘርፍ አመራር ሲወለዱ ተፈጥሮ የጤና ችግር ያለባቸው ህጻናትን ለማገዝ የህክምና አገልግሎቱን ለማሻሻል እና ተደራሽ ለማድረግ ያለውን ጉጉት እዚህ ከመምጣታችን በፊት በተጀመሩ ጥሩ ኢንሼቲቮች መመልከታቸውን ገልጸዋል ፡፡
ከክልሉ ጋር አብረው በመስራት ተጎጂዎችን እናግዛለን ብለዋል ወ/ሮ ቤዛ በሻ በመልዕክታቸው ፡፡
በቢኒያም ገዙ


