
የማዕከላዊ ኢትዮጽያ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ ለተከታታይ 15 ቀናት የሚቆይ የድጋፍ እና ክትትል ስምሪት ሰጠ ፡፡
የ2017 የሁለተኛ ግማሽ ዓመት ማጠቃለያ ድጋፋዊ ክትትል ከ16/10/17 ዓ/ም ጀምሮ ከዞን እና ልዩ ወረዳ ጀምሮ እስከ እስከ ታች ጤና ተቋማት በመውረድ ለተከታታይ አስራ አምስት ቀናት የድጋፍ ክትትል ስራ እንደሚሰራ በኦረንቴሽኑ ተገልጿል ፡፡
የማዕከላዊ ኢትዮጽያ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ ስምሪት በሰጡበት ወቅት እንዳሉት ድጋፍ እና ክትትሉ በ2017 ዓ/ም የነበሩ ጥንካሬዎች የሚለዩበት ለ2018 ዓ/ም ስራ ግብዓት የሚሰበሰብበት በመሆኑ በልዩ ትኩረት እንዲደረግ አሳስበዋል ፡፡
በዘርፉ የተቀመጡ የጤና የልማት እና ኢንቨስትመንት ግቦችን ለማሳካት ክልሉ ያለበትን ደረጃ ለማወቅ የሚያስችል እንዲሆን መዋቅሮቹ ያሉበት ደረጃ እስከታች ድጋፍ እንዲደረግ አሳስበዋል ፡፡
በመጀመሪያው ዙር የክልሉ ድጋፍ እና ክትትል በተካሄደበት ጊዜ በክልል ምላሸ እንዲሰጥ የተነሱ የጤና ተቋማት ግንባታ ችግሮች ፣ ለመአጤመ ከፌደራል የተመደበ ብር ፈጥኖ አለማውረድ ፣ የመድሀኒት እና የህክምና ቁሳቁሶች ችግሮች በአብዛኛው መዋቅሮች መነሳታቸው በስምሪቱ ተገምግሟል ፡፡
አሁን ላይ በሁሉም መዋቅሮች የተቋረጡ ግንባታዎች እንዲሁም አዳዲስ ግንባታዎችን ማስጀመር መቻሉ ፣ ለመአጤመ ከፌደራል የተመደበ ሀብት እንዲወርድ መደረጉ ፣ የመድሀኒት ችግርን ለመፍታት 18 የመሀበረሰብ መድሀኒት ቤቶች ግንባታ እየተጠናቀቀ መሆኑ እንዲሁም የህክምና ቁሳቁስ ለመፍታት የተደረጉ ጥረቶች በክልሉ ምላሽ ማስገኘታቸው ተመላክቷል ፡፡
ድጋፍ እና ክትትት ሲጠናቀቅ ከዞን ጀምሮ በየደረጃው ግብረመልስ በመስጠት የመጀመሪያ ዙር ድጋፍ እና ክትትል ላይ የተሰጠ ግብረመልስ መሻሻሎች መኖራቸውን እያረጋገጡ መዋጣት እንደሚገባም በስምሪት ኦረንቴሽኑ ላይ ተገልጿል ፡፡



