
ወባን በመከላከል ረገድ የሚታየውን መዘናጋትና የትኩረት ማነስ ችግር በመቅረፍ በመጪው ክረምት ሊከሰት የሚችለውን የወባ ጫና ለመቀነስ በሚደረገው ጥረት ውስጥ ሁሉም አካላት ርብርብ እንዲያደርጉ የክልሉ ጤና ቢሮ ጥሪ አቀረበ።
ቢሮው ክልል አቀፍ የወባ መከላከል ስራዎችን በሀላባ ቁሊቶ እየገመገመ ነው።
(ሆሳዕና፣ሰኔ 2/2017) ፣ ወባን በመከላከል ረገድ የሚታየውን መዘናጋትና የትኩረት ማነስ ችግር በመቅረፍ በመጪው ክረምት ሊከሰት የሚችለውን የወባ ጫና ለመቀነስ በሚደረገው ጥረት ውስጥ ሁሉም አካላት ርብርብ እንዲያደርጉ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ጥሪ አቅርቧል።
ቢሮው ያለፉትን አስር ወራት ክልል አቀፍ የወባ መከላከል ስራዎች አፈጻጸም ግምገማ በሀላባ ቁሊቶ እያካሄደ ይገኛል።
በዚሁ ወቅት እንደተባለው ባለፉት ጥቂት አመታት ወባን በመከላከል ረገድ ወባን በመከላከል ረገድ የታየው መዘናጋትና የትኩረት ማነስ ችግር በሽታው ከፍተኛ ጫና እንዲያስከትል አድርጎታል ።
የቢሮው ምክትልና የጤና ፕሮግራሞች ዘርፍ ሃላፊ አቶ አሸናፊ ጴጥሮስ እንዳሉት በተለይ ከጥቂት አመታት ወዲህ የወባ በሽታ ሁለንተናዊ ጫናና ሞት እየጨመረ መጥቷል።
ይህም በታየው ትኩረት ማነስ ምክንያት መሆኑን ጠቁመው የመዘናጋት ሁኔታው ለወባ ስርጭት ምቹ የሆኑ አካባቢዎች መበራከትና ከአየር ሁኔታው ተቆራኝቶ ሰፊ ችግር መፍጠሩን አብራርተዋል ።
ይህ ሁኔታም በ2030 ወባን ለማጥፋት እየተደረገ ባለው ጥረት ላይ ጫና እንደሚፈጥር አቶ አሸናፊ ተናግረዋል ።
በክልሉም በአሁኑ ወቅት የወባ ጫና መስፋቱን ያነሱት ምክትል የቢሮ ሃላፊው በያዝነው ክረምት ሊከሰት የሚችለውን የወባ ጫና አስቀድሞ ለመከላከል ሁሉም አካላት የተቀናጀ ርብርብ ሊያደርጉ ይገባል ብለዋል።
ወባ የመከላከል ስራዎች ህዝቡን ባሳተፈ መልኩ ተጠናክረው እንዲቀጥሉም አሳስበዋል ።በተለይም አካባቢን በማጽዳት፣የአጎበር አጠቃቀምን በማሳደግና የህዝቡን ግንዛቤ ማሳደግ ተግባራት ሊጠናከሩ እንደሚገባ ገልጸዋል ።
የጤና መዋቅር በግብኣት አቅርቦት፣በኬሚካል ርጭት፣በበሽታ ቁጥጥርና ክትትል ተግባራት እንዲሁም በህክምና አገልግሎት ላይ በልዩ ትኩረት መስራት እንደሚጠበቅበት አስረድተዋል ።
የክልሉ መ/ኮ/ጉ/ቢሮ ነው



