Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሁለተኛ ዙር የተቀናጀ የፖሊዮ ክትባት መስጠት ተጀመረ::

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሁለተኛ ዙር የተቀናጀ የፖሊዮ ክትባት መስጠት ተጀመረ

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ የተቀናጀ የፓሊዮ ክትባት ዘመቻ ክልል አቀፍŕ ማስጀመሪያŕ መርሃ ግብር በጠምባሮ ልዩ ወረዳ አስጀምሯል።

በክልሉ ከግንቦት 22 እስከ 25/2017 ዓ/ም እድሜያቸው ከ5 ዓመት በታች ለሆኑ ህፃናት ቤት ለቤት በሚሰጠው ክልል አቀፍ የተቀናጀ የፓሊዮ ክትባት ዘመቻ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር በጠምባሮ ልዩ ወረዳ ዱርጊ ቀበሌ ጤና ኬላ ላይ ተካሂዷል።

መርሃ ግብሩን ያስጀመሩት የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል ሀላፊና እና የህብረተሰብ ጤና እንስትቲዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ማሙሽ ሁሴን እንደገለፁት በክልሉ በሁሉም መዋቅሮች በሁለተኛው ዙር የተቀናጀ የፓሊዮ ክትባት ዘመቻ ከ1,1 ሚሊየን በላይ ህፃናትን ለመከተብ መዘጋጀታቸውን ጠቁመዋል

ከፓሊዮ ክትባት ጎን ለጎን መደበኛ ክትባት ያልተከተቡና ጀምረዉ ያቋረጡ ህፃናትን ለይቶ መከተብ፣በተፈጥሮ የቆልማማ እግር፣ የከንፈርና የላንቃ መሰንጠቅ ችግር ያለባቸው ህፃናት ልየታ፣የፌስቱላና የማህፀን ዉልቃት፣የማህፀን በር ጫፍ ካንሰር ያጋጠማቸዉ እናቶችን ለይቶ በነፃ ህክምና እንዲያገኙ ለማድረግ የሁሉም ባለድርሻ አካላት ሚና የጎላ ነው ብለዋል።

የፖሊዮ በሽታ በአብዛኛዉ የሚከሰተዉ ከፅዳት ጉድለት እና ጥራትን ካልጠበቀ የክትባት አሰጣጥ ችግር ነው ያሉት አቶ ማሙሽ የአከባቢን ንጽህና በመጠበቅ እና ሜዳ ላይ መፀዳዳትን ካቅምን እንዲሁም ጥራት ያለዉ ክትባት ከሰጠን የፖሊዮ በሽታ ይጠፋል ብለዋል አቶ ማሙሽ።

በክልሉ በሁሉም መዋቅሮች በተመሳሳይ የክትባት ዘመቻው መሰጠት መጀመሩን የገለፁት አቶ ማሙሽ በየቀኑ በሚሰጠው የክትባት ዘመቻ ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡም ጥሪ አቅርበዋል

እንጂነር ሀብታሙ በላይነህ የጠምባሮ ልዩ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ በበኩላቸዉ ክትባት ማስከተብ የህፃናትን ህመምና ሞት እንዲሁም የአካል ጉዳት ለመቀነስ የጎላ ፋይዳ እንዳለዉ ገልፀው የሚሰጠውን ክትባት በተገቢው በመዉሰድና የአከባቢያችንን ንጽህና በመጠበቅ የፖሊዮ በሽታን መከላከል እንደሚገባ አሳስበዋል።

አቶ ተከስተ ሳሙኤል የጠምባሮ ልዩ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት ሀላፊ በእለቱ እንደተናገሩት በ2ኛ ዙር የተቀናጀ የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ ከ25ሺህ በላይ ህፃናትን ቤት ለቤት ለመከተብ ሙሉ ዝግጅቱ መጠናቀቁን ገልፀዋል

አቶ ተከስተ አክለዉም ለዘመቻው ስኬታማነት የሀገር ሽማግሌዎች፣የሃይማኖት አባቶችና በየደረጃው ያሉ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ አሳስበዋል።

በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ የክልል፣ የዞን እና የልዩ ወረዳ ከፍተኛ አመራሮች ፣ የአጋር ድርጅት ተወካዮች ፣የሚዲያ አካላት፣የጤና

ባለሙያዎች ፣ የአካባቢው ነዋሪዎችና የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።

በሸምሲያ አደም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *