Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

የክልሉ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ላቦራቶሪ ምርመራ አገልግሎት ተመርቆ በይፋ ሥራ ጀመረ።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አንተነህ ፈቃዱ እና የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሳሮ አብደላ የክልሉ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ላቦራቶሪ ምርመራ አገልግሎት መርቀው በይፋ ሥራ አስጀመሩ።

ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎቹ የክልሉ ጤና ቢሮ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ላቦራቶሪ አገልግሎት በይፋ ሥራ ያስጀመሩት በወራቤ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ተገኝተው ነው።

በዕለቱም የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተደድር፣ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አንተነህ ፈቃዱ፣ የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሳሮ አብደላ፣ የማዕከላዊ ኢትዮጽያ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ ፣ የማዕከላዊ ኢትዮጽያ ክልል ጤና ቢሮ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ማሙሽ ሁሴን ፣ የስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘይኔ ቢልካ፣ የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊዎች ፣ የዞን መምሪያ ኃላፊዎች እና ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል።

በአብርሃም ሙጎሮ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *