Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

የክልሉን ጤና ለማሻሻል እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን ለማጠናከር ድጋፉን እንደሚያጠናክር የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ገለጸ ፡፡

የክልሉን ጤና ለማሻሻል እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን ለማጠናከር ድጋፉን እንደሚያጠናክር የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ገለጸ ፡፡የኢትዮጽያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ለማዕከላዊ ኢትዮጽያ ክልል ጤና ቢሮ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩነት ድጋፍ አደረገ ፡፡

የኢትዮጽያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ጌታቸው ቶሌራ እና ቡድናቸው በማዕከላዊ ኢትዮጽያ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በመገኘት የተለያዩ ድጋፎችን አድርገዋል ፡፡

በጉብኝቱ ከህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩቱ ባለሙያዎች ጋር ውይይት የተደረገ ሲሆን ኢንስቲትዩቱን ለማጠናከር የተለያዩ የኮምፒዩተር ፣ ሰርቨር እና ሞደም ድጋፎችን አድርገዋል ፡፡

የኢትዮጽያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ሁለት ኮምፒዩተር ሁለት ሞደም እና ሰርቨር ድጋፍ ባደረገበት ወቅት ንግግር ያደረጉት የኢትዮጽያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ጌታቸው ቶሌራ ኢንስቲትዩቱ የክልሉን የጤና ዘርፍ በምርምር በቴክኖሎጂ እና በተያያዥ ዘርፎች ድጋፉን እንደሚያጠናክር ገልጸዋል ፡፡

ዶክተር ጌታቸው አያይዘው ዛሬ የተደረገውን ድጋፍ ሊፕ ከሚባል አጋር ድርጅት ያገኘውን መሆኑን ጠቅሰው በቀጣይ ከተቋማም አጋሮቻቸው እና ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመቀናጀት ክልልሉን ለመደገፍ እንደሚሰሩ አስታውቀዋል ፡፡

በጤና ቢሮ የክልሉ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ማሙሽ ሁሴን በበኩላቸው ለተደረገላቸው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበው ዛሬ የተደረገው ድጋፍ አጋዥ መሆኑን ጠቅሰው ክልሉ አዲስ በመሆኑ እየተደረገ ያለው ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል ፡፡

በኢትዮጽያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዶክተር ማስረሻ

ቡድኑ የክልሉ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት eoc ማዕከል ፣ በቅርቡ ተመርቆ አገልግሎት የጀመረው የክልሉ ላብራቶሪ በመዘዋወር ጉብኝት አድርገዋል ፡፡

በውይይቱ የኢንስቲትዩቱ የጥናት እና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክተር ዶክተር ስናፍቅ አየለ ለተሳታፊዎች በኢንስቲትዩቱ እና ዳይሬክቶሬቱ የተሰሩ ስራዎች የታለፉ ተግዳሮቶች ለተሳታፊዎቹ ቀርቧል ፡፡

በድጋፍ እና ጉብኝቱ የኢትዮጵያ እና የክልሉ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ለገሰ ጴጥሮስን ጨምሮ ዳይሬክቶሬቶች እና ባለሙያዎች ተገኝተዋል ፡፡

በቢኒያም ገዙ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *