Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

የኤች አይ ቪ ኤድስን ለመከላከል እና መቆጣጠር ዘርፉ የቅኝት እና ምላሽ ስራዎች ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ተገለጸ ፡፡

የኤች አይ ቪ ኤድስን ለመከላከል እና መቆጣጠር ዘርፉ የቅኝት እና ምላሽ ስራዎች ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ተገለጸ ፡፡

የማዕከላዊ ኢትዮጽያ ክልል ጤና ቢሮ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የኤች አይ ቪ ኤድስ የዘጠኝ ወር ቅኝት እና ምላሽ ፕሮግራም አፈጻጸም ግምገማ በመካሄድ ላይ ነው ፡፡

በጤና ቢሮ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የጤናና ጤና ነክ ድንገተኛ አደጋዎች ቅኝት እና ምላሽ ዴይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶወልደሰንበት ሸዋለም በመክፈቻ ንግግራቸው እንደገለጹት የኤች አይቪ ኤድስ ቅኝት እና ምላሽ ፕሮግራም ከ2012 ዓ/ም ጀምሮ ወደ ሙሉ ተግባር ከገባ በኃላ በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን ገልጸዋል ፡፡

ኤች አይ ቪ ኤድስን ለመከላከል እና መቆጣጠር የዘርፉ ቅኝት እና ምላሽ ስራ በከፍተኛ ደረጃ ማገዙን ገልጸዋል ፡፡

በዘጠኝ ወሩ የኤች አይ ቪ ኤድስ የቅኝት እና ምላሽ ስራችን በጥንካሬ እና መሻሻል በሚገባቸው ጉዳዮች ላይ በጋራ የምንመክርበት እና ለቀጣይ ምን መስራት አንዳለብን የምንለይበት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

አቶ ወልደሰንበት በክልሉ eoc በየ ሳምኝቱ የኤች አቪ ቪ ኤድስ ቅኝት ስራ እየተገመገመ የመጣ መሆኑን ገልጸው የመረጃ ጥራት ጉዳይ በቀጣይም ትኩረት ተሰጥቶ መሰራት እንደሚገባ አስታውቀዋል ፡፡

በቢኒያም ገዙ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *