Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል “የጤና ዘርፍ አርበኝነት ለሀገር እድገት” በሚል መሪ ቃል የጤና ባለሙያዎች ውይይት ተካህዷል፤

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል “የጤና ዘርፍ አርበኝነት ለሀገር እድገት” በሚል መሪ ቃል የጤና ባለሙያዎች ውይይት ተካህዷል፤

ሆሳዕና፦ግንቦት -7-2017ዓ.ም

በክልሉ በሁሉም የጤና ተቋማትና ሆስፕታሎች ውይይት የተደረገ ሲሆን ዋና ዓላማው በጤና ልማት ዘርፍ የተመዘገቡ ስኬቶችና እየተስተዋሉ ያሉ ጉድለቶችን እንዲሁም ቀጣይ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮችን በመለየት ከዘርፉ ባለድርሻ አካላት ጋር የጋራ መግባባት መፍጠር ነው።

ባለፋት አመታት መንግስት በማህበራዊ ልማት ዘርፍ በተለይም የጤና አገልግሎት ተደራሽነትና ጥራትን ለማሳደግ በትኩረት እየሰራ የቆየ ሲሆን ተጨባጭ ለውጥ መመዝገቡ በወይይቱ ተነስቷል።

በጤና ልማት ዘርፍ የሚስተዋሉ የተለያዩ የሰው ኃይል፣ የግብዓት፣ የአገልግሎት አሰጣጥና የመልካም አስተዳደር ጉድለቶችን ደረጃ በደረጃ ለሟሟላት ሰፊ ጥረት እየተደረገ መሆኑንና አሁንም ያሉ ችግሮችን ለመቅረፍ መንግስት ቁርጠኛ መሆኑ ተገልጿል፣

በተለያየ መልክ ከአፈጻጸም አንጻር የሚታዩ ጉድለቶች ሁሉም የሴክተሩ ባለድርሻ አካል የየድርሻውን ወስዶ ማሻሻል እንደሚገባ መግባባት ላይ ተደርሷል።

በቀጣይም የጤና ባለሙያዉ በሀገር ደረጃ የተቀረጸዉን አዲሱን የጤና ልማት ፖሊሲ ለመተግበር በሚደረገዉ ጥረት የራሱን አስተዋጾ ለማበርከት ቃል በመግባት ዉይይቱ ተጠናቋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *