Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

ለማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የመጀመሪያ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት ላብራቶሪ የምርመራ አገልግሎት ስራ ዛሬ በይፋ ተጀምሯል፡፡

ለማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የመጀመሪያ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት ላብራቶሪ የምርመራ አገልግሎት ስራ ዛሬ በይፋ ተጀምሯል፡፡

ለማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የመጀመሪያ የሆነው የሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት ላብራቶሪ የምርመራ አገልግሎት ይፋዊ ስራ ማስጀመሪያ በወራቤ ኮምፕርሄንሲቭ ሰፔሻላይዝድ ሆስፒታል ተጀምሯል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ እና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አንተነህ ፈቃዱ እና በኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር የላብራቶሪ አገልግሎት አስተባባሪ ዶ/ር ሳሮ አብደላ የምርመራ አገልግሎት መስጫው መረቀው ስራ አስጀምረዋል።

በክልሉ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ግርማ ወንድሙ በምረቃው ሰነስረዓት እንዳሉት የላብራቶሪዉ ስራ መጀመር በተለያዩ መንገድ የሚከሰቱ የጤና እክሎችን በህክምና አገልግሎት መከላከል ያስችላል፡፡

የኤች አይ ቪ ኤድስ ፡ የቲቪ ምርመራ ዉጤቶችን በአጭር ዉስጥ በመለየት ለታካሚዎች ተገቢ የህክምና አገልግሎት ለመስጠት እንደሚረዳም ተናግረዋል፡፡

እንዲሁም ተላላፊና ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎችን በአግባቡ ለማሰራትና የደም ዉጤት ለማምጣት በተለያዩ ክልሎች ይከሰት የነበረን የተገልጋዩን እንግልት እንደሚያስቀርም ነው ያስረዱት፡፡

ለምርመራ የሚያስፈልጉ ማሽኖችን ከኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩትና ግብረ ሰናይ ድርጅቶች መገኘቱን ጠቅሰዉ ፡-ላብራቶሪዉን ለማደራጀት ብቻ 10 ሚሊየን ብር በጀት ከክልሉ መንግስት ድጋፍ ተደርጓል ብለዋል፡፡

በመርሐ ግብሩ ላይ የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ ፡ የክልሉ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት ዋና ዳይሬክተር ማሙሽ ሁሴንን ጨምሮ የክልል ፡ የዞን ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *