
የማዕከላዊ ኢትዮጽያ ክልል ጤና ቢሮ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በህብረተሰብ ጤና መረጃ ጥንቅር እና ትንተና ላይ ያተኮረ ስልጠና ለኢንሰሸቲትዩቱ ባለሙያዎች በሆሳዕና መስጠት ተጀምሯል፡፡
ስልጠናውን በንግግር የከፈቱት የማዕከላዊ ኢትዮጽያ ጤና ቢሮ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ለገሰ ጴጥሮስ የመረጃ ስርዓትን በዲጂታል ቴክኖሎጂ እንዲታገዝ ማድረግ መረጃ በአንድ ቋት በማከማቸት እንደ አገር ውሳኔ ለመስጠት ያገለግላል ብለዋል ፡፡
በክልሉ ያሉ ሆስፒታሎች የዲጂታል አሰራሮችን በመተግበር ከወረቀት ነጻ አገልግሎት መስጠት መጀመራቸው የክልሉ የጤና አስተዳደር ስርዓት እንዲሻሻል እያደረገ መምጣቱን ገልጸዋል ፡፡
የዲጂታል ዳታ ትንተና እና ቅመራ ስራ ከዚህ በፊት በአለም ጤና ድርጅት ድጋፍ የሚሰራ መሆኑን ገልጸው አሁን በራስ አቅም መጠቀም እንዲቻል ታስቦ የተዘጋጀ ስልጠና መሆኑን አስታውቀዋል ፡፡
ስልጠናው የክልሉ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የባለሙያዎቹን በዲጂታል ቴክኖሎጂ በታገዘ የዳታ መተንተን መተርጎም ብቃት ለማሳደግ መሆኑ በስልጠናው ተገልጿል ፡፡
በአብርሃም ሙጎሮ



