
ሆሳዕና ሚያዝያ 08/2017ዓ.ም
የዕለቱ የክብር እንግዳና የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የዴሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ቀድሩ አብደላ ባስተላለፉት መልዕክት በክልሉ የወጣቶች ክንፍ በበጀት ዓመቱ ከዝግጅት ምዕራፍ ጀምሮ ተግባራት የተመሩበት አግባብ ዘርፈ ብዙ ውጤቶች የተመዘገበቤት አግባብ ነው ያለው።
ብልፅግና ፓርቲ በትውልድ ሽግግር የሚያምን ፓርቲ ነው ያሉት አቶ ቀድሩ የወጣቶች ክንፍ የወጣቶች ድምፅ የመሆን ተልዕኮውን እየተወጣ ለወጣቱ ሁለንተናዊ ብልፅግና እውን ለማድረግ የክንፉን ተግባራትን በከፍተኛ ኃላፊነት እየተወጣ እና በንቅናቄ የሚፈፀሙ የንቅናቄ ተቋማት የተግባር አፈፃፀም የተሻሉ አፈፃፀሞች እንድመዘገቡ ወጣቶች ሚናቸውን መወጣታቸው አመስግነዋል።
ወጣቶች በጤናው መስክ ተላላፊና ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች ላይ በቅድመ መከላከል ሥራ ለሚደረገው ጥረት ስኬትና የአመለካከት ግንባታ ላይ በየደረጃው ባለው በክንፉ አደረጃጀት በትኩረት ልሰራ ይገባል።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ጽህፈት ቤት ሃላፊ ወጣት አብዱ ድንቁ የንቅናቄ ስራዎቹን ልዩ ዕቅድ አቅርበዋል።
ወጣት አብዶ በሚቀጥሉት ወራት ከብልጽግና ፓርቲ ጎን በመሆን በንቅናቄ እና በፖለቲካ ዘርፍ የሚሰሩ ስራዎች የክንፉ አባላት ግንባር ቀደም ተሳታፊነት የንቅናቄ ስራዎች፣ ድጋፍና ክትትል የሚደርግባቸው ዋና ዋና ተግባራት ለተሳታፊዎች በዝርዝር አቅርበዋል።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ የማህበረሰብ ጤና ድንገተኛ አደጋዎች ክትትልና ምላሽ ዳይሬክተር አቶ ወልደሰንበት ሸዋዓለም የወባ በሽታ አሁናዊ ሁኔታን በተመለከተ ለተሳታፊዎች ሰነድ በማቅረብ በጉዳዩ ላይ ውይይት ተደርጓል።
በመድረኩ ከዞን፣ ከልዩ ወረዳና እና ከከተማ አስተዳደር የተወጣጡ የክንፉ አመራሮች ተሳትፈዋል።



