
የማዕከላዊ ኢትዩጲያ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢንስትቲዩት ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ማሙሽ ሁሴን ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች ለስቅለትና ለትንሳኤ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በዓሉን ስናከብር መላው ህዝባችን ራሱን ከተላላፊ እና ተላላፊ ካልሆኑ በሽታዎች ሊጠብቅ ይገባል በተለይም ወቅቱ ዝናባማ በመሆኑ ከወባ፣ ከኮሌራ፣ ከኩፍኝ በሽታዎች ራሱን ለመጠበቅ በየአካባቢው ከሚገኙ ጤና ባለሙያዎች የሚሰጠውን ምክር መቀበል፤ አጎበር በአግባቡ መጠቀም፣ በየአካባቢው ያቆረ ውሃን ማፋሰስ፣ በሜዳ ከመፀዳዳት መቆጠብ፣ ክትባት ህፃናትን በአግባቡ ማስከት እንደሚገባ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡
በዓሉን ስናከብር ሌላው ትኩረት ሊሰጥ የሚገባው ተላላፊ ያሉኑ በሽታዎችን ነው ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ በተለይም ለወራት ከቅባት ነክ ምግቦች የራቀውን የአመጋገብ ሥርዓታችንን ቅባት ወደ በዛባቸው ምግቦች ስንሸጋገር በጤናችን ላይ ችግር እንዳይፈጥር መጠንቀቅ እንደሚገባ አንስተዋል ።
በድጋሚ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን አደረሳችሁ! በዓሉ የሠላም፣ የፍቅር፣ የይቅርታ፣ የመቻቻል፣ የአብሮነትና የወንድማማችነት እንዲሆንም መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።
መልካም በዓል!!
