Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

የጤና ቁጥጥር ባለሙያዎች ደንቦችንና መመሪያዎችን ተከትለው እንዲሰሩ ጥሪ ቀረበ።

የጤና ቁጥጥር ባለሙያዎች ደንቦችንና መመሪያዎችን ተከትለው እንዲሰሩ ጥሪ ቀረበ።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ የጤና ቁጥጥር ባለሙያዎች ደንቦችንና መመሪያዎችን ተከትለው እንዲሰሩ ጥሪ አቀረበ።

የክልሉ ጤና ቢሮ ጤናና ጤና ነክ አገልግሎቶችና ግብዓቶች ጥራት ቁጥጥር ባለሥልጣን በጤናና ጤና ነክ አገልግሎቶች ላይ ለጤና ተቆጣጣሪ ባለሙያዎች በሆሳዕና ከተማ ሲሰጥ የነበረው የ3 ተከታታይ ቀናት ስልጠና ተጠናቋል።

የቢሮው ምክትል ኃላፊና ጤናና ጤና ነክ አገልግሎቶችና ግብአቶች ጥራት ቁጥጥር ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካ አለሙ ስልጠናውን ባጠቃለሉበት ወቅት እንደተናገሩት የጤና ቁጥጥር ባለሙያዎች ደንቦችንና መመሪያዎችን ተከትለው እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል።

የጤና ቁጥጥር ሥራ ቁርጠኝነት ይፈልጋል ያሉት ዳይሬክተሩ የዘርፉ ባለሙያዎች በተመደቡበት ለህዝባቸው ንጽህና በተሞላ መንገድ እንዲሰሩ አሳስበዋል።

ሰልጣኞች ከዚህ ስልጠና በኋላ በቁጥጥር ሥራዎቻቸው የሚታይና ተጨባጭ ውጤት ማስመዝገብ እንዳለባቸው አቶ ፋሲካ አስገንዝበዋል ።

ከክልሉ የተወጣጡ የጤና ቁጥጥር ባለሙያዎች በሰጡት አስተያየት የተሰጠው የአቅም ግንባታ ስልጠና የቁጥጥር ስራዎችን በአግባቡ እየሰራን ነው ወይ ብለን ራሳችንን እንዲንጠይቅ ያደረገ ነው።

ከስልጠናው መነሻ ደንቦችንና መመሪያዎችን ተከትለን መሥራት እንዳለብን በቂ እውቀት አገኝተናል ነው ያሉት ሰልጣኞቹ።

ስልጠናው በተለምዶ የምንሰራቸውን የጤና ቁጥጥር ተግባሮችን በህግና መመሪያ መሠረት እንዲንሰራ ያስችላል ሲሉም ገልጸዋል።

የወሰድነውን ስልጠና መሠረት በማድረግ ለማህበረሰባችን ሞዴል የሆኑ የጤና ቁጥጥር ሥራዎችን ለመከወን እንተጋለን ሲሉም ተደምጠዋል።

በአብርሃም ሙጎሮ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *