
የሰርዓተ ምግብ ግብዓት አጠቃቀም ስርዓት ላይ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት ከባለድርሻ አካላት ጋር ያለውን ቅንጅት በማጠናከር መስራት ይገባል ሲሉ የማዕከላዊ ኢትዮጽያ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ ገለጹ ፡፡
የክልሉ ጤና ቢሮ የስርዓተ ምግብ ላይ የተሰሩ ስራዎች የስምንት ወር አፈጻጸም ግምገማ በወራቤ ከተማ መካሄድ ጀምሯል ፡፡
በመድረኩ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ በስርዓተ ምግብ ስርዓት ላይ ከሁሉም ሴክተሮች ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል ፡፡
መንግስት የስርዓተ ምግብ እና ምግብ ችግርን ለመፍታት ስራዎችን እየተሰራ መሆኑን አንስተዋል ፡፡
ስርዓተ ምግብ ላይ የሚታየውን ክፍተት ለመሙላት የግብዓት አቅርቦት ከመንግስት በተጨማሪ በአጋር አካላት እየተደረገ መሆኑን ጠቅሰው በአጠቃቀም ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት ህብረተሰቡን ባለቤት ማድረግ እንዲሁም ቢሮው በህግ ምላሽ ለመስጠት እየሰራ መሆኑን አስታውቀዋል ፡፡
በጤናው ዘርፍ እየተሰራ ባለው ስራ ተደራሽነትን እና ሽፋን ለማሳደግ እየተሰራ ባለው ስራ በጥሩ ደረጃ እንደሚገኝ ገልጸው የአገልግሎት ጥራት እና ተጠቃሚነትን ይበልጥ ለማረጋገጥ ትኩረት አድርጎ መስራት ይገባል ብለዋል ፡፡
አቶ ሳሙኤል በመክፈቻ ንግግራቸው ሌላው አጽንኦት የሰጡት የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራምን ስራን እስከ ቀበሌ በማድረስ
የሴቶች ልማት ህብረትን እና ቤተሰብ ደረጃ ማውረድ ትኩረት እንዲሰጥ አሳስበዋል ፡፡
በመድረኩ የር/መ/ር እንዳሻው ጣሰው የኢኮኖሚ አማካሪ ረ/ፕሮፌሰር አንተነህ መሉን ጨምሮ የጤና ፣ የንግድ እና ገበያ ቢሮ ምክትል ኃላፊዎች ፣ የዞን የልዩ ወረዳ እንዲሁም የወረዳ እና ከተማ ጤና ኃላፊዎች ተገኝተዋል ፡፡
በቢኒያም ገዙ




